Get Mystery Box with random crypto!

በሰዎች ፊት ንግግር የማድረግ ፍራቻ አለበዎት? መድረክ ላይ ንግግር የማድረግ ፍራቻ ሰባ አምስት | 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

በሰዎች ፊት ንግግር የማድረግ ፍራቻ አለበዎት?

መድረክ ላይ ንግግር የማድረግ ፍራቻ ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነውን የዓለማችንን ሕዝብ እንደሚፈትን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ዮድሊ የተባለው የድረ-ገጽ መድረክ ይህን ፍራቻዎን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዘው ያስወግዱ ዘንድ መፍትሔ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሰዎች ሊያቀርቡ ያሰቡትን ንግግር በኮምፒዩተራቸው ካሜራ እና ማይክሮፎን አማካኝነት በድረ-ገጹ መጠቀሚያዎች ይቀርጻሉ፡፡

ድረ-ገጹም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተ-ቀመሮች አማካኝነት በንግግሩ ውስጥ የሚገኙ አላስፈላጊ ቃላትን፣ ፍጥነትን፣ የድምፅ መለያየት እና ሌሎች ክፍተቶችን በአሁናዊ ቅፅበት ይጠቁማል፡፡

ከእርስዎ የሚጠበቀው ስህተትዎን እያረሙ ንግግርዎን ደጋግመው በመለማመድ ፍራቻዎን የሚያስወግድ የራስ መተማመን መሰነቅ ብቻ እንደሆነ ዚ.ዲኔት ዘግቧል፡፡

የTEDx አሰልጣኞች፣ የንግግር ፕሮፌሰሮች እና በሕዝብ ፊት በሚደረጉ የንግግር ውድድሮች አሸናፊ ግለሰቦች በስራው ሂደት በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡ የጉግል፣ ፌስቡክ እና አፕል የቀድሞ ኢንጅነሮች ደግሞ መድረኩን በማበልፀግ ሂደት መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ አጋዥ መጠቀሚያዎችን ያካተተው ድረ-ገጽ መቀመጫውን ሲያትል ባደረገው አለን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አማካኝንት የበለፀገ ነው፡፡

እርስዎም የንግግር ልምድዎን የማሻሻል ሀሳቡ ካለዎት www.yoodli.ai ያለምንም ክፍያ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
EAll

   |  - @tom_abe - |