Get Mystery Box with random crypto!

#GAT የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ' 62 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል | ትምህርት ሚኒስቴር

#GAT

የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

" 62 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National GAT) የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።

በዚህም መሠረት ፤ አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች #ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።

* ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከላይ ተያያዘውን ደብዳቤ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር ማረጋገጡ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister