Get Mystery Box with random crypto!

'ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ክፍል ትደግማላቸሁ' በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን | ትምህርት ሚኒስቴር

"ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ክፍል ትደግማላቸሁ" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች የ2014 የትምህርት ዘመን የማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ሆን ብለው ተማሪዎችን ለማዘናጋት ዘንድሮ ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም የሚል ሀሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ገልጿል።

መረጃው ፍጹም ከእውነት የራቀ እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዘ ከትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የሌለ መሆኑን ቢሮው አረጋግጧል።

በተመሳሳይ "ሁሉም የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል የሚዘዋወረው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የተቋሙን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ማየቱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በመሆኑም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቀው ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER