Get Mystery Box with random crypto!

#የ8ኛ_ክፍል_ፈተና በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይ | ትምህርት ሚኒስቴር

#የ8ኛ_ክፍል_ፈተና

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።

ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡

የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል አብራርተዋል።

ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ መታወቁን ብስራት ኤም ሬድዮ ዘግቧል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER