Get Mystery Box with random crypto!

#ScholarshipTip የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድ | ትምህርት ሚኒስቴር

#ScholarshipTip

የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 ሊሆን ይገባል።

አመልካቾች እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜው ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://a2ascholarships.iccr.gov.in

@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER