Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አ | ትምህርት ሚኒስቴር

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ
አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሚያዚያ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

የማመልከቻ ካምፓሶች፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዘንዘልማ ካምፓስ፣
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በይባብ ካምፓስ፣ የተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ በመምህርነት
ተማሪዎች በሰላም ካምፓስ

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መጠቀም ይቻላል።

ለምዝገባ ወደ ተቋሙ ስትሄዱ መያዝ የሚገባችሁ፦

• የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ውጤት ዋናውና ኮፒ
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በሌላ በኩል በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER