Get Mystery Box with random crypto!

ገቢራዊ እየሆነ የሚገኘው አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ የምልክት ቋንቋን አለማካተቱ በክፍተትነት ሊታይ እ | Tikvah-University

ገቢራዊ እየሆነ የሚገኘው አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ የምልክት ቋንቋን አለማካተቱ በክፍተትነት ሊታይ እንደሚገባ ተገለፀ።

መንግሥት አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ማዋሏ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊሲው የምልክት ቋንቋን ሳያካትት ቀርቷል።

ይህም በሰነዱ አካታችነትን ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትምህርት፣ ቋንቋና መስማት የተሳናቸው ባህል ጥናት ክፍል ኃላፊ ጳውሎስ ካሱ (ዶ/ር) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በምልክት ቋንቋ ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ የመምህራን መመሪያና የተማሪዎች መማሪያ መፃሕፍት ቢዘጋጁም፤ በስርዓተ ትምህርቱ የምልክት ቋንቋን አለመካተቱ በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚፈጥረው ክፈተት ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች የምልክት ቋንቋ በኢትዮጵያ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ ሆኖ ዕውቅና እንዲያገኝ ጥያቄ እያቀርቡ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ #መናኸሪያ_ሬዲዮ

@tikvahuniversity