Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር ለ 50,000 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡ | Tikvah-University

ትምህርት ሚኒስቴር ለ 50,000 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

በመጪዎቹ ሐምሌ እና ነሐሴ ወራት የሚሰጠው ስልጠናው፤ የቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

42,000 መምህራን ለ120 ሰዓት እንዲሁም 8,000 የትምህርት አመራሮች ለ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

መምህራኑ በሚያስተምሩበት ትምህርት ውጤታማነታቸውን የሚጨምር የማስተማር ስነ-ዘዴ (ፔዳጎጂ) ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ ፈተና እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

@tikvahuniversity