Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች” በተሰኘ ጭብ | Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

ውይይቱ ዛሬ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡

መርሐግብሩን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ምሁራን በመድረኩ በአቅራቢነትና ተወያይነት ይሳተፋሉ፡፡ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

@tikvahuniversity