Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቀርከሃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሒዳል፡፡ 'Cl | Tikvah-University

#ጥቆማ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቀርከሃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሒዳል፡፡

"Climate-smart Bamboo Forest Economy for Sustainable Development” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የሚመክረው ጉባኤው፤ ሚያዝያ 11 እና 12/2016 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡

ቀርክሃ ከምግብነት እስከ ቤት ውስጥ መገልገያ እቃ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ እንዲሁም ለቢዝነስ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው አረንጓዴ ወርቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ሄክታር የተፈጥሮ ቀርክሃ ሃብት እንዳላት የሚገመት ሲሆን በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የቀርክሃ ሃብት ይገኛል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሔደው ጉባኤ፤ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች እና ተመራማሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity