Get Mystery Box with random crypto!

Dambi Dollo ትላንት በደረሰ የመኪና አደጋ ሦስት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ህይወት | Tikvah-University

Dambi Dollo

ትላንት በደረሰ የመኪና አደጋ ሦስት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ህይወት አልፏል፡፡

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ 'አይራ ቅርንጫፍ' የዕረፍት ቀናት (Weekend) ትምህርት አስተምረው ሲመለሱ የነበሩ መምህራን ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ሁለት መምህራን እና አንድ አሽከርካሪ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ላለፈ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ዛሬ ጠዋት የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሠራተኞቹ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን በመግለፅ፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

@tikvahuniversity