Get Mystery Box with random crypto!

#Update * የቅጣት ውሳኔ ማሻሻያ ! የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረ | TikvhaEthiopia

#Update

* የቅጣት ውሳኔ ማሻሻያ !

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ፤ " ያቀረብኩትን የፍቅር ጥያቄ አልተቀበለችም ፣ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ ውጪ ልትወጣ ነው። " በሚል ስሜት ተነሳስቶ ተማሪ ጽጌረዳ ግርማይን አካል 9 ጊዜ በስለት ወጋግቶ የመግደል ወንጀል ፈፅሟል።

በቀድሞው አጠራር የጋሞ ዞን ዐቃቤ ህግ የመሠረተውን የወንጀል ክስ ተመልክቶ ግራና ቀኙን ሲያከራክር የቆየው የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በቀን 19/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ውስኖ እንደነበር ይታወሳል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ሲከታተል ቆይቷል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የበየነው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ባለመገኘቱ የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አሻሽሎ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ22 ዓመት ፅኑ እሥራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

ምንጭ ፦ የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን