Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ከተማ የሚገኙ 300 ቤቶችና የንግድ ተቋማት በእሳት ወደሙ። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለ | TIKVAH-MAGAZINE

በአንድ ከተማ የሚገኙ 300 ቤቶችና የንግድ ተቋማት በእሳት ወደሙ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ፤ ሮብ ገበያ ከተማ ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ300 በላይ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ደርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸው ተገልጿል።

የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኮማንደር በጋሻው ሽባበው ቃጠሎውን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያልተቻለው በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ አውሎ ነፋስ እንደነበርና ቤቶች ተጠጋግተው በመሰራታቸው እንደሆነ ነው የገለጹት።

እንደ ኃላፊው ገለፃ በቃጠሎው የደረሰውን የንብረት ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ተጣርቶ በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልፀው ወቅቱ በአከባቢው ነፋስ የሚበዛበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።

የወረዳው አደጋ መከላከልና መልሶ ማቋቋም ክትትል ባለሙያ አቶ አንባየ ይግዘው በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም ግብዓት በነፃ ማቅረብና ብድር ሊመቻችላቸው እንደሚችል ተናግረዋል ሲል ወረዳው አስታውቋል፡፡

በእሳት ቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው የህብረሰብ ክፍሎችም እለታዊ የምግብ ፍጆታና ቁሳቁሶች እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

መረጃው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine