Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል Fig | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥቆማ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር #ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመልስ ያለመ ነው።

ስለሆነም እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሆስፒታሉ ጥሪ አቅርቧል።

አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሰዎች #Share በማድረግ እናድርስ

@tikvahethmagazine