Get Mystery Box with random crypto!

የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በኢትዮ | TIKVAH-MAGAZINE

የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል

በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ከመስማት ጋር የተገናኘ ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል።

የምልክት ቋንቋዎች የራሳቸው ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት እና ዘዬ ያላቸው የተሟሉ፣ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ ከውልደት ጀምሮ መስማት ለተሳናቸው ሕጻናት ደግሞ ብቸኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ነው፡፡

ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በዚህም የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባት።

የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸውን የተሳትፎ መጠንና የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ብሎም ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉና ውጤታማ በሆነ ደረጃ እንዲረጋገጡ ለማስቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ሙሉ ጹሑፉን ለማንበብ https://ehrc.org/expertview

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethmagazine @RWethiopia