Get Mystery Box with random crypto!

#DireDawa: ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከ | TIKVAH-MAGAZINE

#DireDawa: ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ

መጋቢት 15 ቀን በምሽቱ ፈረቃ ለሥራ የወጣው አሽከርካሪ ወጣት መኮንን ግርማ  አቶ መሀመድ ዑስማን የተባሉ ተሳፉሪን  ከሳቢያን ወደ ኦርቢት ያደርሳል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ ተደውሎ ይጠየቃል።

አሽከርካሪው እንደተባለው ከተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለት በላስቲክ የተጠቀለለ በርካታ ብር ተቀምጦ ማግኘቱን እና ወዲያው ገንዘቡን ይዞ ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳሬክቶሬት በመምጣት 150ሺህ ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ተናግሯል።

ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ዑስማን ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የምሽት ባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውንና፣ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋና ማቅረባቸውን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል።

ስለ ድሬዳዋ የምሽት ባጃጆች እንቅስቃሴ አዲስ ዘይቤ የድሬዳዋ የሌሊት ሾፌሮች ትላንት እና ዛሬ ከሚለው ጹሑፍ ማንበብ ይቻላል።

@tikvahethmagazine