Get Mystery Box with random crypto!

2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉ ተገለጸ የብሔራዊና የክልል የጸ | TIKVAH-MAGAZINE

2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉ ተገለጸ

የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 759 ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን በ175 ጥቆማዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በ81ዱ ላይ የክስ መዝገብ ማደራጀቱን እና የክስ መዝገብ በተደራጀባቸው መዝገቦች ውስጥም 640 ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን አሳውቋል።

እስከ አሁን በተደረጉ የማጣራት ሥራዎችም 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ባላቸው የመንግሥትና የሕዝብ ኃብት ላይ ጉዳት መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን በሌላ በኩል 25,885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ተጠቁሟል።

ይህ የተባለው የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት የጋራ የአፈጻጸም ግምገማ በሚካሄድበት መድረክ ነው።

@tikvahethmagazine