Get Mystery Box with random crypto!

ትዊተር የሩሲያ፤ቻይና እና ኢራን መሪዎችን በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያወጣ እንደሚገኝ የአውሮፓ | TIK TOK አዲስ

ትዊተር የሩሲያ፤ቻይና እና ኢራን መሪዎችን በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያወጣ እንደሚገኝ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ፡፡

ህብረቱ ትዊተር የሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጫ አውድ እየሆነ መጥቷል ሲል ከሷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ባለቤትነቱ የኤለን መስክ የሆነውን ትዊተርን የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨ ነው ያለሲሆን በተያያዘም ስለ ሩስያ የተዛቡ መረጃዎችን እያወጣ ይገኛል ሲል አስጠንቅቋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት የሴቶች ጉዳይ ፕሬዝደንት ቬራ ጆሮቫ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት ትዊተር ስለ ክርሚሊን እያሰራጨው ያለው መረጃ በሩስያ የሚፈፀመውን ወንጀል ለመደበቅ የሚመክር ነው ብለዋል፡፡


በአዲሱ የዲጅታል አገልግሎቶች ህግ በአውሮፓ ህብረት ጥብቅ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው 19 የዲጅታል መረጃ መለዋወጫ መድረኮች መካከል ትዊተር አንደኛው ነው፡፡

ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት በለንደን የተቋቋመ ኤ.ፒ.ኤ የተሰኘ የምርምር ተቋም በቅርቡ ባጠናው ጥናት ትዊተር የሩሲያ፤ቻይና እና ኢራን መሪዎች በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያወጣ እንደሚገኝ በጥናት ተረጋግጧል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

#በዩሐንስ አበበ

@Arada_Fm