Get Mystery Box with random crypto!

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

የቴሌግራም ቻናል አርማ tibyaan54 — 💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!
የቴሌግራም ቻናል አርማ tibyaan54 — 💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!
የሰርጥ አድራሻ: @tibyaan54
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.17K
የሰርጥ መግለጫ

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው።
«السلفية منهجي»
https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 21:37:02
ቢጨከን ህፃን ላይ ይጨከናል ማን ይታመናል ታዳ ስራ ውለህ/ሽ ቤትሽ ልጆችሽ ናፍቀውሽ ስትደርስ/ሺ ይህ ቢገጥምሽ ምን ትሆናለህ/ኛለሽ
ምን አይነት ዘምን ላይ ደረስን ኢላሂ አሁን ይቺንም መንግስት አስሮ ይቀልባትና ከዛ በይቅርታ ይለቃታል አይደል አይ ኢስላም ለዚህ የሚሰጠው ፍርድ ፍትህን የጠበቀ ነበር ምን ያደርጋል አላህ ከዚህ ፈተና ይጠብቃቹ
ያማል

አዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ እያለቀስች ነው
ህዝቡ በሙሉ ያየውን ማመን አቅቶታል



ቦሌ አራብሳ ብሎክ 51 ሁለት ህፃናት በሰራተኛ ታርደዋል

አንዷን አርዳ
አንዱን አንቃ ነው የገደለችው

ህፃናቱ ወንድም ና እህት ናቸዉ

ሰራተኛዋ ለፖሊስ እጇን ሰጥታለች

እናት ከስራ ስትመጣ ልጆቿ ታርደዉ ነዉ ያገኘችዉ::
209 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:17:12 #ዋናው_ልብና_ስራ_ነው

ነቢያት የተላኩት፣ ቁርኣንና መሰል መጽሐፍትም
የወረዱት የሰው ልጆችን ልብ ለማጽዳት፣ ስራና ስነምግባርን ለማስተካከል ነው።

ያለንበት ዘመን ከመቼውም በላይ ሰዎች ውስጣቸውንና ከጌታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከማስተካከል ይልቅ ውጫቸውን በማሳመርና ለሰዎች እያስመሰሉ መኖር የበዛበት ዘመን ነው።

አላህ ከሁሉም በፊት ከሰው ልጆች የሚያየው ልብና ስራን ነው።

ልብ አላህን ከፈራና ንጹህ ከሆነ፣ ስራም መልካም ከሆነና ለአላህ ተብሎ ከተሰራ የሰው ልጅ አላህ ዘንድ ደረጃው ከፍ ይላል፤ ይከብራልም።

ልብ ከቆሸሸና አላህ በሚጠላቸው ነገሮች ከተሞላ፣ አካላትም ለመጥፎ ስራዎች ከተንቀሳቀሱ የሰው ልጅ ጌታው ዘንድ ክብር ያጣል፤ ኣኺራውንም ይከስራል።

ለሰዎች ማስመሰሉና የውጩ ብቻ ማማርም አላህ ዘንድ ምንም አይጠቅመውም።

ሐዲሡም "አላህ መልክና ገጽታችሁንም ይሁን ሀብታችሁን አያይም።ይልቅ የሚያየው ልብና ስራችሁን ነው" ነው የሚለው።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ሀሙስ 04/2/1444 ዓ.ሂ

@ዛዱል መዓድ
~~~~
በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ

https://telegram.me/ahmedadem
~
https://t.me/zad_qirat
~~~~
https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
287 views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:51:17

255 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:11:17 የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
40 views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:28:11
37 views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:28:11 ታላቅ የሙሓደራ ዝግጅት
     በፉሪ በድር መስጂድ


የሙሓደራ ርዕስ

1/የላኢላሀኢለላህ ማብራሪያና ትሩፋት

በኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ

2/የቤተሰብ ዋልታና ማገር

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

ቦታ ፡- ፉሪ በድር መስጂድ

ቀንና ሰዓት:-እሁድ ሰፈር 8/1444 ዓ.ሂ  
      ወይም ነሐሴ 29/2014

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

በዕለቱ የተለያዩ ኪታቦችን ቀርተው የተፈተኑ ሴት ተማሪዎችና የክረምት ኮርስ የተከታተሉ ተማሪዎች ይመረቃሉ፤ ይሸለማሉ።

@ዛዱል መዓድ
36 views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:04:38
185 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:52:49
«የወራቶች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መፅሐፍ
ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት
ወር ነው።አራቱ የተከበሩ ናቸው።»

https://t.me/ibrahim_furii
187 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:57:00 ኡስታዝ አህመድ ኣደም ሐፊዘሁላህ ቆየት ካሉ ሙሓደራዎቹ ውስጥ በጣም ገሳጭ የሆነ ሙሓደራ
አንዘርቱኩሙንናር
(እሳትን አስጠንቅቂያቸኋለሁ)

https://t.me/ahmedadem/1858
119 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:02:47
137 views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ