Get Mystery Box with random crypto!

#ያኔ_እኔን_አያርገኝ አንቺ ፥ ረሳውሽ ስል ማስታውስሽ፣ ብናፍቅሽ ናይልኝ ብል ማልመልስሽ። አን | ጥበብን በማሾ

#ያኔ_እኔን_አያርገኝ

አንቺ ፥ ረሳውሽ ስል ማስታውስሽ፣
ብናፍቅሽ ናይልኝ ብል ማልመልስሽ።

አንቺ ፥ ደስታ ሳቄን ቀምተሽኝ ፣
ከንቱ ፍጡር አደረግሽኝ፣

#አዎ
ስናፍቅሽ መቼ መጣሽ!
ከሀሳቤስ መቼ ወጣሽ?

#ብቻ
ናፍቄሽ ሳትመጪ ፥ ጠብቄሽ ስትቀሪ፣
ሁኛለሁ አለሜ ፥ ተስፋ ቢስ በራሪ፣

#አየሽ
በመሄድሽ ብስራት ፥ ሲናወጥ መንፈሴ፣
ሲንቀጠቀጥልሽ ፥ አካልና ነብሴ፣

#አንቺ_ግን?
ህመሜም አልገባሽ፣
ጭራሽ በኔ አነባሽ።

#ብቻ
ጭካኔሽ አይሎ ፥ እርቀሽ ብትሄጂ፣
የኔን ገላ ረስተሽ ፥ ከሌላ ብትለምጂ፣
ያኔ እኔን አያርገኝ አፈር ያርገኝ እንጂ።

#ገጣሚ ሮቤል አለማየው
#ዝምተኛው_ሲርሎስ
2014 ዓ.ም በደሌ