Get Mystery Box with random crypto!

#የጌታዬ_ምፃት . . ቀኑ መሽቶ ጠሀይ ጠልቃ ወጣች ደሞ ውብ ጨረቃ : የጨረቃ መውጣት የጠሀይቷ | ጥበብን በማሾ

#የጌታዬ_ምፃት
.
.
ቀኑ መሽቶ ጠሀይ ጠልቃ
ወጣች ደሞ ውብ ጨረቃ
:
የጨረቃ መውጣት
የጠሀይቷ መግባት
ለማብሰር ቢሆንም ምሽትና ንጋት
:
የሰሞኑ ትንግርት ሆኖብኝ ዱብዳ
ተአምር ያሳየኛል ከሰማይ ሠሌዳ።
:
ዘውትር ሁልጊዜ ከጥልቁ ሰማይ ላይ
ልጇን በእቅፍ እዛ ለሰው መስላ ጠሀይ
ትታየኝ ነበረ የነፍሳችን ሲሳይ።

#ግና ዛሬ.......
ደረሰ መሰለኝ የጌታዬ ምፃት
አየኅት ብቻዋን የጌታዬን እናት።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
በ09/06/2013

#ቻናሌን_ይቀላቀሉ
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho