Get Mystery Box with random crypto!

የማንነትህ መለኪያ “አንድ ሰው ሊያከናውነው በሚችለው የተግባር ልቀት ላይ ገደብ ሊያስቀምጥበት | አሰብህ ሀብታም ሁን (Think and Grow Rich) 0991663602 0939232757

የማንነትህ መለኪያ

“አንድ ሰው ሊያከናውነው በሚችለው የተግባር ልቀት ላይ ገደብ ሊያስቀምጥበት የሚችል ነገር ቢኖር ሰውየው በራሱ ላይ ያለው አመለካከት ነው” – Maxwell Maltz

የትክክለኛው ማንነቴ ዋጋና በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ካልተጣጣመ ወደ ተዛባ የራስ-በራስ ግምት ውስጥ እገባለሁ፡፡ በራስ ላይ ያለ የተሳሳተ ግምት ደግሞ የስነ-ልቦና ቀውሶች ሁሉ ቀንደኛው ነው፡፡ ከዚህ አይነቱ ቀውስ ለመዳን የዋጋን እውነታ በሚገባ ልናጤነው ይገባል፡፡

ማንኛውም ነገር ሁለት አይነት “ዋጋ” አለው፡፡ አንደኛው የዋጋ አይነት አንድ ነገር ከሚሰጠው ጥቅም ጋር፣ እንዲሁም ከእውነተኛ ምንነቱና ማንነቱ ጋር የተያያዘ ዋጋ ነው፡፡ ይህ በእንግሊዝኛው ቫሊው (Value) በማለት ነጥለው የሚገልጹት የዋጋ አይነት ነው፡፡ ሁለተኛው የዋጋ አይነት አንድ ነገር ወደ ገበያ ሲቀርብ የሚለጠፍበት ዋጋ (Price) ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእቃው የምንነትና የጥቅም ዋጋው (Value) ከተለጠፈበት የሽያጭ ዋጋ (Price) ጋር ላይገናኝ ይችላል፡፡ የአንድ ነገር የጥቅሙ ዋጋ ሳይለዋወጥ የሽያጭ ዋጋው ግን አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡

የማንነታችንም ዋጋ ከዚህ ተለይቶ አይታይም፡፡ በአንድ ጎኑ የትክክለኛ ማንነታችንና ሰው የመሆናችን ዋጋ (Value) አለ፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ እኛም ሆንን ሌሎች ሰዎች የለጠፉበትን ዋጋ (Price) አለ፡፡ የሁለቱን ክፍተት በሚገባ በማጤን ማጥበብና ማስተካከል የእኛ ሃላፊነት ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች የማንነታቸውን ዋጋ ካለፈው ታሪካቸው፣ ከወቅቱ ኑሯቸው፣ ሰዎች በእነሱ ላይ ካላቸው አመለካከትና ከመሳሰሉት ሁኔታዎች በመነሳት ይወስኑታል፡፡ የማንነታችን ዋጋ ግን ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ በማንነቴ ዋጋና በተለጠፈብኝ ተመን መካከል ልዩነት ሲኖር የማንነ