Get Mystery Box with random crypto!

ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21

የቴሌግራም ቻናል አርማ theorthodox21 — ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21
የቴሌግራም ቻናል አርማ theorthodox21 — ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21
የሰርጥ አድራሻ: @theorthodox21
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የመዝሙር ግጥሞች እና መፈስን የሚያድሱ መዝሙሮችን መንፈሳዊ ጽሁፎችን
እንዲሁም ህይወትን ይሚለዉጥ መልካም የሆነውን መልዕክት ወደናተ እናደርስ አለን !! @Theorthodox21 ይቀላቀሉን !!
ለማነኛዉም ሀሳብ እና አስተያየት @TiGi21
እንዲሁም መንፈሳዊ መልእክት ማስተላልፍ ለምትፈልጉ
@TiGi21/ @Abraham912 ይላኩልን
እግዚአብሔር ይመስገን !!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 16:10:20
ለመንፈሳዊ ትምህርት ፈላጊዎች
መንፈሳዊ ትምህርት ባሉበት ሆነው በኦን ላይን (Online) መማር እንደሚችሉ ያውቃሉ!
ካላወቁ እንንገሮ! የአንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ት/ክፍል ምዝገባ እያደረገ ይገኛል፡፡
በቀዳማይ ክፍል ትምህርቶች
  ትምህርተ ሃይማኖት
  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  የቤ/ክ ታሪክ
  ክርስቲያና ስነ ምግባር
ትምህርቶች ለተማሪዎች የሚሰጥ ይሆናል!
ለምዝገባ ፡- 
  በሚከተለው የጎግል ፎርም ይጠቀሙ https://forms.gle/VJPVJ2VRMj7Tpddt7 
  በሰ/ት/ቤቱ የንዋያተ ቅዱሳት መገልገያ እቃዎች መሸጫ ሱቅ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
  በሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
  በሰ/ት/ቤቱ የትምህርት ንዑስ ክፍል ቢሮ ከሰኞ እስከ እሁድ
ለበለጠ መረጃ ፡- +251913831400 / +251911112851 / +251969184235
 በቴሌ ግራም https://t.me/anqesbirhanss
አዘጋጅ ፡-  የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
27 views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:01:19 በገና ማለት ምን ማለት ነው

በገና መጀመሪያ የጀመሩት እነማን ናቸው ለምንስ ተጠቀሙበት

የበገና መዝሙር ከበገናው አውታር ወይስ ከእንጨቱ

በገና እንዴት መደርደር እንችላለ?

እንዲሁም ሌሎች የዜማ መሳሪያዋችን መግዛትም ሆነ መለማመድ የምትፈልጉ ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ላላችሁ ያላችሁበት ቦታ እንልካለን።

በተጨማሪም ነፍስን የሚያድሱ መዝሙሮች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ። ለመቀላቀል OPEN የሚለውን ንኩት።




ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█



OMEGA PROMOTION

.
30 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 10:14:20 የነሐሴ ፩፫ ቅዳሴ ምንባብ ቡሄ
(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 9)
----------
28፤ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

29፤ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

30፤ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤

31፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

32፤ ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

33፤ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

34፤ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።

35፤ ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

36፤ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።

37፤ በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።
@ethiopianorthodoxs
260 views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:16:32
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም
316 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:55:40 #የዓርብ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

ድንግል ሆይ! የደናግል ኹሉ መመኪያቸው አንቺ ነሽ፡፡ ከእናንተ መካከል “መመኪያነቷ እንዴት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
፩ኛ) ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “ወበከመ አውፅአ ብእሲ ብእሲተ ዘእንበለ ብእሲት ከማሁ አውፅአት ብእሲት ብእሴ ዘእንበለ ብእሲ ወሀሎ ዕዳ ላዕለ ትዝምደ አንስት፤ ወበእንተዝ ኮነት ፈዳዪተ ዕዳሃ ለሔዋን - ለወንዶች የሚከፈል ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፡፡ ስለዚህም የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) ክርስቶስን ወለደችው፡፡ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደችው፡፡ ድንቅ በሚኾን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ” /ሃይ.አበ.፷፮፥፳፱/፤
፪ኛ) ቀድሞ ወንዶች ሴቶችን በእናንተ ምክንያት ከገነት ወጣን እያሉ ርስት አያካፍሏቸውም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ብእሲ ወብእሲት አሐደ እሙንቱ በክርስቶስ - ወንድም ሴትም የለም፤ ኹላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ብሎ እስኪያስተምር ድረስ /ገላ.፫፡፳፰/ በሔዋን ምክንያት ከገነት ብትወጡ በእመቤታችን ምክንያት ገነት መንግሥተ ሰማያት ገብታችሁ የለምን? ብለው የሚመኩ ኹነዋልና፤
፫ኛ) ደግሞ ለደናግላን አስበ ድንግልናቸውን (የድንግልናቸውን ዋጋ) ስለምታሰጣቸው ሊቁ “ምክሆን ለደናግል” ብሏታል፡፡

ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን፡፡ በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን /ፊል.፫፥፲-፲፩/፡፡ ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሽልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰውን (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል /ዮሐ.፮፥፴፯/፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፬. ድንግል ማርያም ዕፍረተ ምዑዝ (መዓዛው የጣፈጠ) የተባለ ጌታችንን የወለደች ሙዳየ ዕፍረት (የሽቱ መኖርያ) /፩ኛ ሳሙ.፲፥፩ አንድምታው/፤ ዳግመኛም የማየ ሕይወት (የሕይወት ውኃ የክርስቶስ) ምንጭ ናት /መኃ. ፬፥፲፪ አንድምታው/፡፡ የማኅፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ኹሉ አድኗልና፡፡ ከእኛ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አጠፋልን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ኹሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” እንዲል /ቈላ.፩፡፲፱-፳/ በመካከል ኾኖ በመስቀሉ አስታረቀን፡፡ ልዩ በኾነ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ልዩ በኾነ ትንሣኤ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ከእነ አልዓዛር ትንሣኤ የተለየ መኾኑን ለማሳየት ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
፩ኛ) እነ አልዓዛር አስነሺ ይሻሉ፤ እርሱ ግን “ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ብሎ እንደተናገረ /ዮሐ.፲፥፲፰/ የተነሣው በገዛ ሥልጣኑ ነውና፡፡ በተለያየ ሥፍራ “አብ አንሥኦ (አብ አስነሣው)፤ መንፈስ ቅዱስ አንሥኦ (መንፈስ ቅዱስ አስነሣው)” ቢልም አንድ ነው፡፡ ምክንያቱም ዕሪናቸውን መናገር ነውና፡፡
፪ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ በብሉይ ሥጋ ነው፤ የእርሱ ግን በሐዲስ ሥጋ ነው፡፡
፫ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ሞትን ያስከትላል፤ የእርሱ ግን ሞትን አያስከትልም፡፡
፬ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃል፤ የእርሱ ግን አይጠብቅምና፡፡

አዳምን ዳግመኛ ወደ ገነት ከመለሰ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፭. አንዳንድ ተረፈ ንስጥሮሳውያን እንደሚሉት ንጽሕት ድንግል ማርያም ላቲ ስብሐትና “ወላዲተ ሰብእ” አይደለችም፤ የታመነች አምላክን የወለደች ናት እንጂ፡፡ የመናፍቃን መዶሻ የተባለው፣ በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት የካደውን ንስጥሮስን የረታው ቅዱስ ቄርሎስ እሳተ መለኮት አምላክን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ የተሸከመች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የፈጠረውን ፍጥረት የሚመግበው አማኑኤልን የድንግልና ጡቶቿን ወተት የመገበችውን የወላዲተ አምላክን ክብር ያልተረዱትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን ሲወቅስ “ወለዛቲ እንተ መጠነዝ ዐባይ ጾረት መለኮተ እፎ ይከልእዋ እምክብራ ለወላዲተ አምላክ ወላዲተ አምላክኬ ቅድስት ድንግል - ይኸንን ያኽል ታላቅ ኾና መለኮትን የተሸከመችቱን የአምላክ እናት ክብርን እንደምን ይነፍጓታል፤ ይከለክሏታል፡፡ የአምላክ እናት ማለት ድንግል ማርያም ናታ” በማለት የተሰጣትን ክብር በማድነቅ አስተምሯል /ተረፈ ቄርሎስ/፡፡

እንዲህም ስለኾነ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢባሉ ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፤ እርሷ ግን “ማእምንት ሰአሊተ ምሕረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” /ዮሐ.፪፥፩-፲፩/፡፡ ሰአሊተ ምሕረት ሆይ! ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡


ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ

https://mekrez.blogspot.com/2013/08/blog-post_1585.html?m=1

@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
300 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:52:53 የጾም ትርጉም በቤተ ክርስቲያን

የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡-

ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከልበት መከልከል ነው፡፡

አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡

ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ፈቅዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥጋን ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ማዘጋጀት ማብቃት ነው፡፡
ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ15፣564

በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ጾም ከክፉ ሐሳብ፣ ከክፉ ሥራ ማሰብም መራቅም ነው።

ጾም እግርና እጅን፣ ልብንና ሕሊናን ከመጥፎ ቦታዎች ማቀብ /ወደ መጠጥ ቤት፣ ጭፈረና ዘፋኝ ቤት፣ ጥንቆላና ባዕድ አምልኮ ከመትወስድ መንገድ የምትከለክል ናት።

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡

ጾም ለፈቃደ ሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡

ጾም ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለመልምበት ስንቅ ነው፡፡

ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ናት።

ጾም ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው፣ የጸሎት ምክንያት /እናት/፣ የእንባ መገኛ ምንጭ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡
@ethiopianorthodoxs
370 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 08:32:12
1.2K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 07:27:29 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬ ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም መታሰቢያና በዓለም ሁሉ በስሟ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ የተጀመረበት ቀን ነው::

ከሁሉ አስቀድሞ ይኸቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች::

ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከአመኑ ሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቍርባን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያን አልነበራቸውም::

ስለዚህም ጉዳይ አገልጋዮችም ምእመናንም ወደ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልዕክትን ላኩ::

ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም አንሰራም:: ነገር ግን የምንሰራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት ከተመለሱ አሕዛብ ጋር አዘዙአቸው::

በሱባዔው ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸላቸው::

ከሩቅ ያሉም ሐዋርያት ደመና ጠቅሰው ተሰባሰቡ:: ጌታም ባረካቸው:: እንዲህም ብሎ ነገራቸው ይህቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ የፈቀድኩባት ቀን ናት አላቸው::

ይህንንም ብሎ ከከተማው በስተ ምሥራቅ በኵል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያናቱንም ቦታና መሰረቷን ወሰነላቸው::

ከሐዋርያትም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ:: የቤተ ክርስቲያኒቱም ሕንፃዋ እስኪፈጸም ድረስ ደንጊያዋች በሐዋርያት እጅ ውስጥ ይለመልሙ ነበር::

ቤተ ክርስቲያኗ ስታልቅ ጌታ ከሐዋርያት ጋር ቀድሶ አቀበላቸው ኋላም ባርኳቸው ዐረገ::

ይህም የሆነው ዛሬ ሰኔ ሃያ አንድ ቀን ነው:: ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ ቤተ ክርስቲያን መታነጽ ጀመረ::

እኛም ኢትዮጵያውያን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን ማነጽ ጀመርን::

ልመናዋ በረከቷም ከሁላችን ጋራ ይኑር ፍቅሯን በልባችን ጠዐሟን በአንደበታችን እምነቷን በእምነታችን ትህትናዋን በሁላችን ላይ ያሳድርብን ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
1.0K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 09:37:42
"እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ #ሕይወትን_ምረጥ፤"
(ኦሪት ዘዳግም 30፥19) @ethiopianorthodoxs
786 views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 08:41:01 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት 20-25 በነዚህ ቀናት በደብረ ምጥማቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በመንፈስ ቅዱስ ተመልተው አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በታላቅ ቃል አመሰገኗት::

ብዙዎችም ደስታቸውን ወሰን አልፋ ያለቅሱ ነበር::

ብዙዎችም እሷ ለሰጣቸው አምላካቸው ይሰግዱ ነበር::

ብዙዎችም በፍጹም መንፈሳዊ በሆነ ፍቅር ይተቃቀፉ ነበር::

ስለ ድንግል ማርያም ክብር በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ጧፍ ሻማ ችቦ አብረትው እልል ይሉ ነበር::

ስለ ሁሉ ነገር ይህን ያደረገላቸውን አምላካቸውን እያመሰገኑ ይዘምሩ ነበር::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: እኛም በመንፈሰ እግዚአብሔር ተሞልተን ቅድስት ድንግልን ለማመስገን ያብቃን::

ለዚህም ነው አንዳንዶች መንፈሰ እግዚአብሔር በውስጣቸው ስለሌለ በስንፍና ቃል በድፍረት በእመቤታችን ላይ የሚናገሩት::

እኛ ግን ከነሱ የተለየን ነን እናመሰግናታለን እናከብራታለን::

አንደ ሙሉ ጤነኛ ሰው እንደ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር እንደተላከው፤ እንደ ቅድስት ኤልሳቤት በመንፈስ ካልተሞላ በስተቀር እመቤታችንን ሊያመሰግናት የሚከፈት አንደበት አይኖርም።

መንፈሰ እግዚአብሔር ካላደረበትም ለእመቤታችን ሊያሸበሽብ የሚችል እግርም ሆነ እጅ አይኖረውም፤ ለእመቤታችንም የጸጋ ስግደት ሊሰግድም የሚታጠፍ ጉልበት አይኖርም::

ክብርና ምስጋና ለልጇ ይሁን::

ከኃጢአታችን በንሰሐ ሳሙና ታጥበን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተሞልተን እመቤታችንን ለማመስገን ያብቃን ለዘላለሙ አሜን::

የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ስም ከፀሎትና ከተማፅኖ ውጪ ልንጠራት አይገባም።
ሥዕለ ማርያምን ከተቀደሰና ከከበረ ቦታ ውጪ በየትም ሥፍራ ልናስቀምጠው አይገባውም።
ሥዕለ ማርያምን ካህን ከሆኑ ዕጣን ያጥኖታል፣ ምእመን ከሆኑ መልካም ሽቱ ይቀቧታል በምስጋናም ይማፀኗታል።
በሥዕለ ማርያም ፊት ውሸትና ከንቱ ንግግር ሙዜቃና ጭፈራ ሲጋራና ጥንባሆ ሊያጨሱባት አይገባውም።
ሥዕለ ማርያም ቤቶ ኗራ አስታራቂ ሽማግሌ አይፈልጉ እንኳን ከተጣላ ሰው ከፈጣሪ ታማልደን ታስታርቀን የለ!
@ethiopianorthodoxs
1.4K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ