Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ ሺኖዳ ይህን ጽፈው ነበር:: በአንድ ሀገር ዝናብ ጠፋ:: ሰዎች ሁሉ ተጨነቁ:: በመጨረሻም ም | SUCCESS MIND

አቡነ ሺኖዳ ይህን ጽፈው ነበር::
በአንድ ሀገር ዝናብ ጠፋ:: ሰዎች ሁሉ ተጨነቁ:: በመጨረሻም ምሕላ ለማድረግ ተወሰነ:: ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤተ ፀሎት ጉዞ ጀመረ:: አንዲት ሕፃን በጉዞው መካከል ጃንጥላ ይዛ ነበር::
ለምን እንደያዘች ስትጠየቅ እንዲህ አለች :-
"የምንሔደው ዝናም እንዲዘንብ ልንለምን አይደል? ታዲያ ስንመለስ በምን እንጠለላለን?"
ስለዚህች ሕፃን እምነት በዚያን ቀን ዝናብ ዘነበ::
ሕዝቡ ሲደበደብ እርስዋ ጥላ ይዛ ነበር::
አንድን ነገር ከማድረጋችን በፊት እንደሚሳካልን ማመን ተገቢ ነዉ!


መልካም ቀን