Get Mystery Box with random crypto!

TheDeepThingsOfGod

የቴሌግራም ቻናል አርማ thedeepthingsofgod — TheDeepThingsOfGod T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thedeepthingsofgod — TheDeepThingsOfGod
የሰርጥ አድራሻ: @thedeepthingsofgod
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.92K
የሰርጥ መግለጫ

Glorious Church the bride of Christ.
Rapture ready!

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-01 07:08:13 ወዳጄ አሁን ዓላማ ከሌለህ ተኝተህ አትዋል፣ ከአንዱ ማህበራዊ ድረገጽ ወደሌላው ስትገባና ስትወጣም አትዋል፣ ጌም ስትጫወት ወይም ፊልም ስታይም አትዋል! ዓላማህን እስክታገኝ ድረስ ዓላማህን ማግኘትን እራሱን ዓላማህ አድርገው።

መጸለይ ጀምር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀምር፣ ሌሎች ጠቃሚ መጽሐፍት ማንበብ ጀምር፣ ማሰብ እና ማሰላሰል ጀምር፣ መጻፍ ጀምር! ዓላማህን ማግኘትን ዓላማህ አድርገው ያኔ ሕይወት ይጀምራል!

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
1.5K viewsVictor, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:06:56 ዛሬ በማለዳ ስለ ዓላማ አስፈላጊነት አሰላስል ነበር እና በድል መኖር የሚፈልግ ሰው ግልጽ ዓላማ መያዝ እንዳለበት ተረዳሁ።

ተወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር በዚህ ሕይወት ድል አድራጊዎች እንድንሆን ይፈልጋል! ስለዚህ ግልጽ ዓላማ ይኑረን! ዓላማ የሌለው ሰው ሁልጊዜ ተሸናፊ ነው፣ ዓላማ የሌላት ሴት ሁልጊዜ ተሸናፊ ናት!
ዓላማ ይኑረን፣ እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ከትንሽ እስከ ትልቅ በዓላማ ይሁን ያኔ አሸናፊዎች ሆነን እግዚአብሔርን ደስ እናሰኘዋለን!

ይሄንን የመጋቢ ታምራት ሃይሌን መዝሙር አዳምጡት፣ ተባረኩ!

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
784 viewsVictor, 04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 19:59:06 የመወሰን ሃይል!
አምናለሁ ይሄ ለብዙዎች መልስ ነው፣ አሁን ወስኑ እና ለማድረግ የተትረፈረፈ ፀጋን ተቀበሉ።


ለመጸለይ፣ ለማንበብ፣ ለመለወጥ፣ ለመቀደስ፣ ለማደግ፣ ለመስራት፣ ከግብ ለማድረስና እግዚአብሔር ደስ ለማሰኘት ወስኑ እና ከመጠን የበዛ ፀጋን ተቀበሉ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም።

እኔ እወስናለሁ እግዚአብሔር ደግሞ ፀጋውን ያቀርባል።

I make the decision and God supplies the grace.
-Bishop David Oyodepo


@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
1.9K viewsVictor, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:58:35 #ቃል#ከቃሉ

ኢሳይያስ 55
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
¹¹ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።


አስተውሉ : የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን መሻት ለመፈጸም ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣ የእግዚአብሔር ሰራተኛ ነው፣ የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን መሻት እንጂ የእኛን ፍላጎት የሚፈጽም በፍጹም አይደለም።
የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን እንዲሰራ ከፈለግን መሻታችንን እንደ እግዚአብሔር መሻት ማድረግ እግዚአብሔር የሚፈልገውን መፈለግ ይኖርብናል፣ ይሄን ስናደርግ ቃሉ ለእግዚአብሔር የሰራው ስራ ለእኛም የተሰራ ስራ ይሆናል።

ጸሎት : የእግዚአብሔር መሻት የእኔም ነው፣ እግዚአብሔር የሚፈልገውን እፈልጋለሁ፣ እርሱ ቅድሚያ ለሰጠው ነገር እኔም ቅድሚያ እሰጣለሁ፣ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወቴ ይሰራል! አሜን።


@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
2.3K viewsVictor, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:41:56 Jesus your presence makes me whole
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
1.3K viewsVictor, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:09:34
ሆሳዕና ያላችሁ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም ዜና ይዤላችሁ መጥቻለሁ!

የፊታችን አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ በ Jesus Kingdom int. Church በተዘጋጀው ፕሮግራም ተገኝታችሁ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል።

አድራሻ: ከኢየሩሳሌም አደባባይ ወደ ዋቸሞ በሚወስደው የኮብልስቶን መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ።
1.5K viewsVictor, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:56:28 ድል ለሚነሳው...

ንጉሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልአኩ ልኮ ለአገልጋዮቹ በገለጠው ራዕይ በግልጽ እና በተደጋጋሚ እንደምንመለከተው የተስፋ ቃል የተሰጠው ድል ለሚነሱ ባሪያዎች ብቻ ነው---

“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።”
— ራእይ 2፥7 (አዲሱ መ.ት)

“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል የሚነሣም በሁለተኛው ሞት ከቶ አይጐዳም።”
— ራእይ 2፥11 (አዲሱ መ.ት)

“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈበት ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።”
— ራእይ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)

“ድል ለሚነሣና ሥራዬንም እስከ መጨረሻው ለሚፈጽም በአሕዛብ ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም፦”
— ራእይ 2፥26 (አዲሱ መ.ት)

“ድል የሚነሣም እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ እኔም በአባቴና በመላእክቱ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም።”
— ራእይ 3፥5 (አዲሱ መ.ት)

“ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ውስጥ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም። የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም ይኸውም ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ አዲሱን ስሜንም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።”
— ራእይ 3፥12 (አዲሱ መ.ት)

“እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በእርሱ ዙፋን ላይ እንደ ተቀመጥሁ፣ ድል የሚነሣውንም ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።”
— ራእይ 3፥21 (አዲሱ መ.ት)

ተወዳጆች ሆይ ድል መንሳት የግድ ነው፣ የተስፋ ቃል የተሰጠው ድል ለሚነሱ(ለሚያሸንፉ) ብቻ ነው።

ልፍስፍስ እና ተሸናፊ መንፈስ ከዘመናችሁ ላይ በኢየሱስ ስም ተነቀለ፣ በዘመናችሁ ሁሉ ታሸንፋላችሁ።

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
3.9K viewsVictor, edited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:01:29 የተስፋ ቃልን ፍጻሜ የሚቀበሉ ድል የሚያደርጉ ናቸው!

እግዝአብሔር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለተለያዩ ሰዎች የተሰፋ ቃል እንደሰጠ ከቅዱሳት መጽሐፍትና ከራሳችን ልምምድ የምንረዳው ነው፣ እግዚአብሔር ተስፋን የሚሰጥ አምላክ ነው፣ ነገር ግን ተስፋ ከተሰጣቸው ሰዎች የተስፋውን ቃል ፍጻሜ የተቀበሉ እንዳሉ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ፍጻሜ ከመቀበል የዘገዩ እና አንዳንዴም ሰይቀበሉ ዘመናቸው የተፈጸመ ሰዎች አሉ።

ይሄንን እውነት ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ከብዙ ምሳሌዎች ከግብጽ አገር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች ታሪክ መመልከት በቂ ነው፥ 430 አመት በባርነት በግብፅ ምድር ከተሰቃዩ በኋላ እግዚአብሔር ከአባቶቸቻው ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ እና ከያዕቆብ ጋር ያደረገውን ኪዳን አስቦ በጫንቃቸው ላይ የነበረውን ጠንካራ ቀንበር ሰብሮ ከግብፅ አስወጣቸው፣ የሰጣቸው ተስፋ እንደዚህ የሚል ነበር----“ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር --- ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።” — ዘጸአት 3፥8

የተስፋው ቃል "ከግብፃውያን እጅ አድናችኋለሁ፥ ከግብፅም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር አስገባችኋለሁ" የሚል ነው፥ ይህ የተስፋ ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተሰጠ ነው፣ ነገር ግን ከግብፅ አገር ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር የደረሱት ሁለቱ አሸናፊዎች ካሌብ እና እያሱ ብቻ ናቸው የቀሩት ከሚሊዮን የሚበልጡ የእስራኤል ልጆች የተስፋን ቃል ቢቀበሉም ፍጻሜውን ግን ሳይቀበሉ በምድረበዳ ቀሩ።

ካሌብ እና እያሱ የአሸናፊነት መንፈስ ነበራቸው፣ ከነዓን እንዲሰልሉ ከተላኩት መካከል በመልካም ቃል ተናግረው ድልን የሰበኩት ካሌብ እና እያሱ ነበሩ--- “ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ።”— ዘኍልቁ 13፥30 ----አስሩ ተመልሰው የሽንፈት ወሬ በሕዝብ ጆሮ በማውራት የሕዝቡንም ልብ አስፈሩ “ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው ጮኹ፤ ሕዝቡም በዚያ ሌሊት አለቀሱ።”— ዘኍልቁ 14፥1 ---በዚህም ምክንያት የድል ሰባኪዎች እና መሪዎች ከሆኑት ከሁለቱ ሰዎች በስተቀር ጠቅላለው ከግብፅ የወጣው ማኅበር በምድረበዳ ወደቀ፣ ካሌብና እያሱ ግን የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ተቀበሉ ----“እርሱም፦ በእውነት እግዚአብሔርን ፈጽመው ከተከተሉ ከእነዚህ ከቄኔዛዊው ከዮፎኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር፥ ከግብፅ የወጡት ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጥ ዘንድ የማልሁበትን ምድር አያዩም ብሎ ማለ።” — ዘኍልቁ 32፥11-12

የተስፋ ቃል እንደሰማን ፍጻሜውን እንድንቀበል በእግዚአብሔር በመተማመን የአሸናፊነትን መንፈስ እንታጠቅ፣ እጆቻችንን ውጊያ ጣቶቻችንን ጦርነት እናስተምራቸው፣ እንደርሳለን! እንወርሳለን!

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
2.9K viewsVictor, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:09:55 የተስፋን ቃል ፍጻሜ የሚቀበሉ ድል ነሺዎች ብቻ ናቸው!

የተስፋ ቃል የተሰጣቸው ከሚሊዮን የሚበልጡ የእስራኤል ልጆች፣ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ የተቀበሉ አሸናፊ መንፈስ የነበራቸው ሁለቱ የድል ሰባኪዎች እና የድል መሪዎች ብቻ፣ ከሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ከግብፅ ምድር ወጥቶ ከመካከላቸው ከነዓን የገቡት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው!

ተስፋ ፍሬ የሚያፈራው ለድል ነሺዎች ብቻ ነው፣ ከእግዚአብሔር የተስፋ ቃልን የተቀበልን ሁላችንም ተዋግቶ ማሸነፍ የግድ ነው።

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
2.3K viewsVictor, edited  17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 19:45:07 ጥብቅ መልእክት

ሁላችንም እንደምናውቀው ምድር ላይ የተለያዩ ጦርነቶች ተደርገዋል አሁንም እየተደረጉ ነው የእነዚህ ጦርነቶች ዓላማ የተለያየ ቢሆንም በምድር ላይ ያደረሱት ተጽዕኖ ግልጽ ነው፣ አሁን እየተደረገ ያለው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እንኳ በሰፊው ዓለም ላይ የቱን ያህል ጥቁር ጥላውን እንዳጠላ እየተመለከትን ነው፣ ነገር ግን አሁን በቁሳዊው ዓለም ላይ እየተደረጉ ካሉ ጦርነቶች ሁሉ በላይ በምድር ነዋሪዎች ላይ አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ያለ ስውር ጦርነት እየተካሄደ ነው፣ የዚህ ጦርነት ዓላማ ምድራዊ ድንበር ማስፋፋት ወይም ታላቅ ሆኖ መታየት አይደለም፣ የዚህ ጦርነት ዓላማ የተቻለውን ያህል ብዙ ነፍሳትን መግዛት እና የራስ ማድረግ ነው።

ተወዳጆች ሆይ ምድር ላይ እየተካሄዱ ባሉት ውጥረቶች እና የማሳት ዘመቻዎች ትኩረታችን ተበታትኖ ስለነፍሳችን እየተደረገ ያለውን ጦርነት ዘንግተን የሰይጣን ምርኮኛ መሆን አይገባንም።

ስለምን ጦርነት ነው የምናገረው?
ወደዚህ ምድር የመጡ ሰዎችን ሁሉ በሕይወታቸው ዘመን የገጠማቸው ጦርነት አለ፣ አብዛኛዎቹ ተሸንፈው ምርኮኛ እንደሆኑም ይመስለኛል፣ ጦርነቱን የሚያደርገው ሰይጣን ነው፣ የሰዎችን ነፍስ አጥብቆ ይፈልጋል ስለዚህ ወደዚህ ምድር በሚመጡ ሰዎች ላይ ሁሉ መንፈሳዊ ጦርነት ይከፍታል፣ ለማጥቃት የሚጠቀመውም መሳሪያ በዋናነት ስጋዊ ምኞት ነው፣ የሰዎችን የራሳቸውን ስጋዊ ምኞት በመጠቀም ነፍሳቸውን ይዋጋል፣ ነፍሳቸው የእርሱ ምርኮኛ እስክትሆን ድርስ ይዋጋል።

አሁን እኛ ባለንበት ዘመን ሰይጣን ያለውን ሃይል ሁሉ ቀጥሮ እየተዋጋ በመሆኑ ውጊያው በርትቷል፣ ሰይጣን ያለውን ሁሉ ተጠቅሞ የሰዎችን ነፍስ ለማሸነፍ እና የራሱ ለማድረግ እየተዋጋ ነው፣ ብዙዎችም ተሸንፈው እየወደቁ ነው።
ሰይጣን በዚህ ጦርነት አሸናፊ ለመሆን ስጋዊነትን የሚያቀነቅኑ እና የሚያነግሱ ተዋጊዎቹን(በተለያየ መንገድ ለሰይጣን የሚሰሩ ሰዎች) በረዘሙ ተራሮች ላይ አቁሟል፣ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትምና፣ እነሱን እየተመለከተ ትውልዱ ስጋዊ ምኞቱ ተቀስቅሶ እና ተባብሶ ነፍሱን ይወጋል፣ ወደ ልቡ ተመልሶ የማይነቃ ከሆነ የሰይጣን ንብረት ይሆናል፣ ይሄ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የእናንተ መጨረሻ አይሆንም ዛሬ መንቃት ሆኖላችኋል!

ነፍስን ለማሸነፍ እና የራስ ለማድረግ እየተደረገ ያለ ጦርነት አለ፣ ይህንን እውነት በሚገባ መረዳት ጦርነቱን ለመመከት እና መልሶ ለማጥቃት የግዴታ አስፈላጊ ነው።
ተወዳጆች ሆይ በዚህ ጦርነት ውስጥ አሸናፊ እንድንሆን የሚያስፈልገንን የጦር ዕቃ ሁሉ ተሰጥቶናል፣ የእኛ ሃላፊነት የሚሆነው የተሰጠንን የጦር ልብስ መልበስና ተዘጋጅቶ መቆም ነው ---
“ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና።”— ኤፌሶን 6፥13

ወንድሞቼና እህቶች ዛሬ እንንቃ እጃችንን አጣጥፈን ከተቀመጥን እንሸነፋለን፣ የእግዚአብሔር እቃ ጦር ለብሰን ከተዋጋን ግን እናሸንፋለን፣ ብዙዎችን ማዳን እንድንችል ደግሞ ድምጻችን ከተራሮች ላይ ይሰማ።

የእግዚአብሔር ፀጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።
ለመቀላቀል
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
4.4K viewsVictor, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ