Get Mystery Box with random crypto!

ቀናሁ!! የምር ቀናሁ፣ ምሽት ላይ በአውሮፓ ሻንፒዮንስ ሊግ ኢንተር ከ ሲቲ ሲጫወቱ ጨዋታውን እ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

ቀናሁ!!

የምር ቀናሁ፣ ምሽት ላይ በአውሮፓ ሻንፒዮንስ ሊግ ኢንተር ከ ሲቲ ሲጫወቱ ጨዋታውን እየተመለከትኩ ውስጤ በቅናት ይተክናል፣ በማን ቀናህ እንዳትሉኝ፣ በሲቲ ስኬት አልቀናሁም፣ በኢንተር ተፎካካሪነትም አይደለም፣ ቀናት ያንገበገበኝ የአንድሬ ኦናና ብቃት ነው፣ ምናለ የእኛ በሆነ እላለሁ፣ ግብ ክልሉን ጥሎ ወጥቶ፣ በአንድ ፓስ 5 ተጨዋቾችን ሲቀንስ ሳይ፣ በረኛም አልመሰለኝ የተዋጣለት አማካይ እንጂ፣ እንዴት ግን አንድ በረኛ በዚህ ልክ በልበ ሙሉነት ግብ ክልሉን ትቶ ወጥቶ ከአማካዮች በላይ ኳሶችን ያደራጃል፣ እግሮቹ ከጭንቅላቱ ጋር ፍጹም የተናበቡ ናቸው፣ ጫንቅላቱ ያሰበውን እግሩ ይፈጽማል፣ ኳሷን ጠልዟት ያሰበባት ቦታ ነው ቁጭ የሚያደርጋት፣ ብቻ ብዙ ብዙ፣ እንዲህ አይነት ዘመናዊ ግብ ጠባቂ በዩናይትድ እመለከት ይሆን
ቴን ሃግ ንቃ ፕሊስ የቀድሞ ግብ ጠባቂህን ኦናና ከኢንተር አምጣው በቃ አምጣው ኡፍፍፍፍ ይችላልኮ አይገልጸውም!!!

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv