Get Mystery Box with random crypto!

የሁለት ቀኑ እረፍት   ኤሪክ ቴንሀግ ቡድኑ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሰ በኋላ ለተጨዋቾቹ የሁለትቀ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

የሁለት ቀኑ እረፍት  

ኤሪክ ቴንሀግ ቡድኑ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሰ በኋላ ለተጨዋቾቹ የሁለትቀናት እረፍት ለመስጠት ደፍሮ ከተጫዋቾቹ ጋር የተገናኘው ዛሬነው

በዚህ ሲዝን ማንቸስተር ዩናይትድ በሳምንት ሁለት ጌሞችን እያደረገ በቀናት በሳምንታት ልዩነት ብዙ ጌሞችን እያደረገ የተጓዘ ክለብነው ይህ ተደራራቢ ጭዋታን የማድረግ ግዴታ የቡድኑን አቅም እያሳሳው ቀጥሎ መጨረሻው ሲቃረብ በጣም ደካማውን ፍላጎት የሌለውን ተጋጣሚውን ፕረስ ከማድረግ ይልቅ 30 እና 40 ሜትሮችን ለተጋጣሚው በመተው በራሱሜዳ የሚገኝ ቡድን ሁኗል ይህ ድካም ያመጣው ችግር እንደሆነ ግልፅነው

ይህን ድካም ለመቀነስ ቴንሀግ የእረፍት ቀናት ለሁሉም አካል በመፍቀድ እረፍት ከሰጡ በኋላ ዛሬ ወደ ልምምድ የተመለሱ ሲሆን ተጨማሪ ሶስት ቀናትን ጌም ከማድረጋቸው በፊት ያገኛሉ  በሜዳቸው ከ ወልቨስጋር ለሚደረገው ፍልምያ በአካል እና በአእምሮ ተዘጋጅቶ ለመመለስ እረፍት ያስፈልጋል አሁን የሚቀረው ለአሰልጣኙ ታማኝ መሆንና ሜዳለይ መክፈል ብቻነው

ከሰባት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ሰባት ቀናትን ያለጌም የቆዩበት ሳምንት ይህ ሳምንት ብቻነው  ከቀሯቸው አራት ጌሞች ሶስቱን በሜዳቸው ሲጫወቱ ወልቨስ ቼልሲና ፉልሀምን ያገኛሉ ከሜዳ ውጭ ከበርንማውዝጋር ብቸኛውን የሜዳ ውጭ ጌም ያደርጋሉ ከቀሪዎቹ 12 ነጥቦች ዘጠኙን መውሰድ ደሞ የሻምፒዮንስ ሊጉን ተሳትፎ ያስገኛል በተለይ እሁድ ከወልቨስጋር የሚደረገው ፍልምያ የሁሉም ነገር መጀመሪያ በመሆኑ በጉጉት ይጠበቃል

ከዛሬ ልምምድ የተወሰዱ ምስሎችን እነሆ ።


COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv