Get Mystery Box with random crypto!

በአማካኝ በየ ሶስት ቀኑ አንድ ጨዋታ ክለቡ ያደርጋል፣ በኤፕሪል ወር ብቻ ዩናይትድ 9 ጨዋታዎችን | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

በአማካኝ በየ ሶስት ቀኑ አንድ ጨዋታ ክለቡ ያደርጋል፣ በኤፕሪል ወር ብቻ ዩናይትድ 9 ጨዋታዎችን አድርጓል፣ ባለፉት 37 ቀናት ደግሞ 11 ጨዋታዎችን ከውኗል፣ ተጨዋቾች እጅግ ከፍተኛ ድካም ላይ መሆናቸው የማታውን ጨዋታ ማየት በቂ ነበር።

መሮጥ ተስኗቸው እግራቸው ተሳስሮ ተመልክተናል፣ የቴን ሃግ ተደራራቢ ጨዋታዎችን ከግምት ያላስገባ ፍልስፍና በተለይ አሁን ላለው ውጤት እጅግ ተጠያቂውም ነው፣ ብሩኖን ቀለል ያሉ ጨዋታዎች ላይ በማሳረፍ ሳቢትዘርን በሱ በመተካት ማጫወት ይቻል ነበር፣ አንቶኒን በፔሌስትሪ ቢያንስ ቡድኑ ከመራ በኋላም ማሳረፍ ይቻላል፣ ራሽፎርድን በብዙ አማራጭ ማሳረፍም ይቻል ነበር። ከነዚህ ስህተቶች ጀርባ የቫራንና ማርቲኔዝ ጉዳት ክለቡን ጎድቶታል።

አወ የነሱ ቦታ በሊንድሎፍና ሾው ተሸፍኖ ይሆናል፣ ነገር ግን የሾው ወደ መሃል መግባት የዩናይትድን ኮሪደር ጥቅም አልባ አድርጎታል፣ የራሽፎርድ የማጥቃት ሃይል ሾው ባለመኖሩ ተገድቧል።

ብሩኖን እንደ Lb ሆኖ ትናንት ተመልክተነዋል፣ ይህ ደግሞ ዩናይትድ ምን ያህል ምርጫ እንዳጣ ማሳያ ነው።

ተጨዋቾች እጅግ ጫና ውስጥ ናቸው፣ ትናንት ያቺ ጎል ስትቆጠር፣ ራሽፎርድ ራሱን ይዞ ሲተክዝ ብሩኖ ሲበሳጭ ሊንድሎፍ መሬት ሲደበድብ ነበር፣ ከፍተኛ ድካም ከ ጫና ጋር አስቸጋሪ ሆኗል።

ቴን ሃግ ለምን ምን እንዳሰበ ባላውቅም፣ ዩናይትድ ፎረስትን የረታውን ቡድን (አሰላለፍ) ለምን መድገም እንዳልፈለገም አላውቅም።

አንቶኒ ማርሺያልና ፍሬድ ብዙ ጨዋታ ሳያደርጉኳ ከተዳከሙት በላይ ሆነዋል፣ ወደሜዳ ገብተው የሚፈጥሩት የለም።

የአንቶኒ ጉዳይ ሊጉን ካለመድመድ+ተደጋጋሚ ጨዋታ ጥቅሙን አጥፍቶታል፣ ብዙ ብዙ የዩናይትድ ችግሮች ጎልተው የወጡበት፣ ቀጣይ አመት የሚቆየውና የሚሄደው የለየበት ግዜ የፈተና ወር ያለፈውና መጪው ወር ነው!!

በዚህ ቡድን ውስጥ ብዙ ነገር ይታያል! የሚታየው ችግ የሚነቀለው ግን #ሼክ_ጃሲም ኦልድትራፎርድ ከደረሱ ብቻ ነው!!


COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv