Get Mystery Box with random crypto!

የተወዳጇን እና አንጋፋዋ እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ድንገተኛ ዕልፈት በመስማታችን በጣም አዝነናል! | Awtar

የተወዳጇን እና አንጋፋዋ እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ድንገተኛ ዕልፈት በመስማታችን በጣም አዝነናል!

"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እንደነበሩ ይነገራል።
እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከአቶ ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ወይዘሮ ካሣዬ የለምቱ በ1916 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለዱት።በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።
ከትምህርት መልስም በ19 አመታቸው ነበር ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 አመታቸው ምንኩስናን የተቀበሉት።
ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን በወጣትነታቸው ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።
ከ19 84 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ "ቅድስቲቷ ከተማ" ተብላ በምትጠራው እየሩሳሌም አድርገዋል።

አውታር ለቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመድ እና አድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል!

ነፍስ ይማር!!!