Get Mystery Box with random crypto!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋን አስረከበ። አዲስ አበባ፣ ጥር 4 | Awtar

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋን አስረከበ።
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ ከሰባት ዓመታት በፊት ሰጥቷት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ  አስረክቧል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ አርቲስት ማሪቱ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በ2008 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷት እንደነበር ይታወሳል፡፡
አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተሻገረው የሙዚቃ ህይወቷ አራቱን የሙዚቃ ቅኝቶች በመጫወት ትታወቃለች፡፡
በተለይም የአምባሠል ቅኝት አጨዋወቷ የመጠሪያዋ ቅጽል ስም እስከመሆን አድርሷታል ። 

#news  #Awtar #AwtarMusic #musicians #ethiopia #EthiopianMusic #AwtarApp #musiclovers #picoftheday #musiclife #HomeofEthiopianMusic #GetItOnAwtar #MusicForEveryMood #musician