Get Mystery Box with random crypto!

የተዋሕዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido23 — የተዋሕዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido23 — የተዋሕዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @tewahido23
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 159

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-22 19:06:20
14 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 10:19:31 #ለምንድን_ነው_የምንጾመው?

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትርጕሙ ምን ማለት እንደኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

(አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 71-72 - ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

@beteafework      @beteafework
@beteafework      @beteafework
@beteafework      @beteafework
6 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 21:48:33 #ሕርቃል_ማን_ነው? ለምንስ የመጀመሪያው ሳምንት ጾም በስሙ ተሰየመ?

የዐቢይ ጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት (ከዘወረደ እስከ ቅድስት ያለው) የምንጾመው ጾም ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ለመሆኑ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ የመጀመሪያው 7 ቀን ጾም በስሙ ተሰየመ?

ታሪኩ እንዲህ ነው፦ በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡

በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡
5 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 07:35:18 ከምግብና ከመጠጥ ያልተቆጠበ ሰው ለክርስቶስ ሕይወቱን መስጠት እንደሚከብደው ግልጽ ነው። ድፍረት ያላት ነፍስ ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን መግዛት ለሥጋ ፈቃድ የሚያስፈልገውን ምግብና መጠጥ በመተው የሥጋ ፈቃድን ድል መንሳትንና የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላታል። ይህች ነፍስ የሚመጣባትን ከባድ ነገር ሁሉ እስራትም ቢሆን ግርፋትም ቢሆን መቋቋም ይቻላታል።

በእግዚአብሔርና በተጋድሎ የፀኑ ሰዎች ሥጋቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትነትን መቀበል ይቻላቸዋል። በአካላዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን ከመጾም በሚገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ሰማዕታት ጾምን የስልጠና ትምህርት ቤት አድርገውታል። የጾም ቀናት የሚጠቅሙን ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በኃጢአታችን እንድንፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ብቻ ሳይሆን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ያለንን ፍቅር ለመግለጽም ይጠቅሙናል። ሰማዕታት የጾምን፣የፀሎትን እና የብሕትውናን ሕይወት የኖሩ ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዚህችም ዓለም የሚጠቅሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነው"1ኛ ቆሮ 7፥34

እውነተኛ ጾም አንድን ሰው ራሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ያሰለጥነዋል። ቀሪ ሕይወቱን እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲያውቅ ያደርገዋል። ራስን መቆጣጠር ለቅድስና ሕይወት መሠረት ነው። ጾም ቅጣት ሳይሆን ደስታ ነው።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ (የሕይወት መዓዛ)
11 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 07:13:59 “ጾምን አውጁ” (ኢዩ.፪፥፲፭)

እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሰን!

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከሚታወጁት ሰባት አጽዋማት መካከል ታላቅ ለሆነው ለዐቢይ ጾም ስላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው!  

ዐቢይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?

በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹ዐበየ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡ ጾሙም ዐቢይ የተባለበት ሦስት ዓበይት ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ስለሆነ ነው፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፫) በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥና የቀኑ ብዛትም ፶፭ ቀንም ነው፡፡ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሦስቱ ርእሰ ኃጢአት (ትዕቢት፣ ስስት ፍቅረ ነዋይ) በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ጾም ተብሏል፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፲፩)፡፡

የዐቢይ ጾም ስያሜዎች

ዐቢይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ 
ጾመ ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሰፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡  በሰፊ እርሻ የተመሰለበት ምክንያት የቀኑ ብዛት ከሌሎች አጽዋማት ስለሚበዛ ነው፡፡

የካሣ ጾም፡- አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሣ እየተባለ ይጠራል፡፡

የድል ጾም፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡

ጾም አስተምህሮ፡- ዐቢይ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

የዐቢይ ጾም ሳምንታት

ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ ደብረዘይት፣ ገብረ ኄር፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡
 
፩ኛ. ዘወረደ፡- በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን፤ አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
13 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 08:05:15 "ስምምነቱ ተጥሷል፣ ቤተክርስቲያንን ጠብቁ በፀሎትም ትጉ"... ቅድስት ቤተክርስቲያን
++++++++++++++++++++++++++++++++

(የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም
   አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ "አዲሱ ሲኖዶስ" በሚል አዲስ ስያሜ ስምምነቱን የሚጥስ መግለጫ አውጥቷል ስትል ቅድስት ቤተክርስቲያን ገልጻለች።

ቤተክርስቲያን በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን እንገኛለን ስትል  ተደምጣለች።

ከሁለት ቀናት በፊት በተፈጸመው ስምምነት ሰላም ቢፈጠርም አሁን ግን ሃይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል ፤ ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።

ሿሚና ተሿሚ በአስተሳሰባቸውም ሆነ በአነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ አንድ እንደሆኑም ተናግረዋል ፤ 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም "ኤጲስ ቆጶሳት" እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል።

በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ነገሩን ለማጥራት ብንጠብቅም ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ በቤተ ክህነት ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ገብተዋል።

ሆኖም ግን በስምምነቱ መሠረት "የብሔር ብሔረሰቦች ኤጲስ ቆጶሳት" ሿሚዎች ነን ያሉ 3 ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የሰጡትን መግለጫ እስካላስተባበሉ ድረስ ከቤተክህነት እንዲወጡ ይደረጋል ስትል  ቤተክርስቲያን  አስታውቃለች።
5 views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:38:25 Channel photo updated
17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:33:09 በእሥር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን በተመለከተ በጥቂት ቀናት ጉዳያቸው ታይቶ እንደሚፈቱ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
6 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:33:04
'አባ' ሳዊሮስን ጨምሮ ሦስቱ የቀድሞ ጳጳሳት የአሁኑ የሕገ ወጡ ቡድን መሪዎች የይቅርታ ደብዳቤ አቅርበዋል።

እንዲህ ሆነ ቢባልም አይናችንን ወደ ቤተክርስቲያን ጆሯችንን ለቅዱስ ሲኖዶስ ማድረጋችንን አንተው
6 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 21:58:09 በሕገ ወጥ መልኩ የተሾሙት ሰበር መረጃ?!!!
===========
ሕገወጡ ቡድን (የቀድሞ 3 ጳጳሳት እና 25 ሕገ ወጥ ተሿሚዎች) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ቢሮዎች እንዳይገቡ ፍርድ ቤት አግዷል።

እንዲሁም ከመንግሥት የጸጥታ አካላት
1.የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
2.የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
3. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
 ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙት በቤተክርስቲያኗ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንዳይገኙ ሲል ያገደ መሆኑን ተገልጿል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን የሕግ ጥሰት የፈጸሙ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል ብሏል ፍርድ ቤቱ!!
!
14 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ