Get Mystery Box with random crypto!

'ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቼም አትፈርስም!' የስፖርት ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው 'ጥምቀት ፣ ገና እና | TMS

"ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቼም አትፈርስም!"
የስፖርት ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው
"ጥምቀት ፣ ገና እና ፋሲካ በደረሰ ቁጥር እንኳን አደረሳችሁ እያላችሁ አጉል ተወዳጅነትን ለማግኘት የምትሯሯጡ ታዋቂ ግለሰቦች እና ምሁራኖች ለመሆኑ ኦርቶዶስ ተዋህዶን ለማፍረስ ይህ ሁሉ ሲደረግ የት አላችሁ ?
እውቅናውም ሆነ እውቀቱ ከሀይማኖታችን በታች ነው። በዚህ ምድር ላይ ፕሮፌሰር ብትሆን ወይም ዶክተር ፣ ታዋቂ ድምፃዊ ወይም አርቲስት አለያም ታዋቂ ጋዜጠኛ ብትሆን ለስጋህ እንጂ ለነፍስህ አንዳችም ጠብ የሚል ነገር አይኖረውም።
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጉዳይ የጳጳሳት ፣ የካህናት፣ የዲያቆናት ጉዳይ ብቻ አይደለም ። የእያንዳንዳችን የእምነቱ ተከታዮች ሀላፊነት ነው።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቼም አትፈርስም ።