Get Mystery Box with random crypto!

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮ | Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች

ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

በፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ...

1. ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ፣ ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

2 ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/ የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/ እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መግኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

3 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

4 ማንኛውም አደንባዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት) ህክምና መስጫ መርፌ))መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው።

5. ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው።

6. ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው። (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)

7. ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው።

8 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩለት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

9. በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው።

10. በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው ።