Get Mystery Box with random crypto!

#Update መደበኛ ዝውውር 1) ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለጽነው ምክንያት ብንዘገይም በየትኛው | Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹

#Update
መደበኛ ዝውውር

1) ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለጽነው ምክንያት ብንዘገይም በየትኛውም የዝውውር መት ተዛውሮ የማያውቅ በቁጥር ከፍ ያለ 1800 ባለሙያዎች ከቅሬታ በፊት ተዘዋውረዋል።

2) ከብዙ ውጣ-ውረድ በኋላ ዛሬ ፎ-15 ተፈቅዶልን ይኸው የተፈቀደውን ፎ-15 ጭምር አያይዘናል።

3) ዞኖች የባለሙያው ጥያቄ እንዲመለስ በመፈለግ ያሳያችሁትን ትግስት እያመሰገን በዝውውር የሚመጡትንም ሆነ የሚገቡትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድታስተናግዱልን አደራ ማለት እንፈልጋለን።

4) የቅሬታ ጊዜው በቴሌግራም ኦንላይን ስለሆነ እና ቀኑ እንዳይራዘም በሚል ረቡዕ ከሰዓት የመጨረሻ ውጤት ስናሳውቅ የተዘዋወራችሁ በፍጥነት ወደተዛወራችሁበት ተቋም በመሔድ ሪፖረት ማድረግ ነገር ግን ዘግይቶ ለሚሔድ ኃላፊነት ራሱ ይወስዳል።

5) የተዘዋወሩትን ማስቀረት አይቻልም።

6) በጊዜያዊ የተመደቡትን እስከ ቀጣይ ሐሙስ ቋሚ ምደባ በዝውውር ኮሚቴው ምደባ የሚሠጥ ይሆናል።
7) እንደ አምናው ሁሉ በዚህ ዓመትም ሁሉንም የሕክምና ማስረጃ ያጣራን ሲሆን 19 ፎርጅድ አግኝተናል። ከውድድር ውጭ ያደረግን ሲሆን ቀጣይ ክስ የሚመሠረት ይሆናል።
8) ረጅም ዓመታት ያገለገሉ ባለሙያዎች ባሉበት በቋሚነት ከተመደቡ 5ወር የሆነን እያለን ሌላ ባለሙያ ሊዛወርበት አይገባም፤ እኛ ባለንበት መመደብ አለብን” በሚል የቢሮውን መልካም ስራዎች የምታጠለሹ አካላት ተገቢ አለመሆኑን አውቃችሁ ተጠያቂ የምናደረግ መሆኑን እንገልጻለን።

በመጨረሻም እስከመጨረሻው ድረስ ታግሳችሁ 'አይዟችሁ በርቱ ተስፋ እንዳትቆርጡ' ስትሉን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው።

Via DAGNU MEREJA