Get Mystery Box with random crypto!

ከፈጣሪ በታች ለወጣቷ ሐና ሙሉጌታ እንድርስላት ሼር ይደረግ በምስሉ ላይ የምናያት እህታችን ሀ | Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹

ከፈጣሪ በታች ለወጣቷ ሐና ሙሉጌታ እንድርስላት
ሼር ይደረግ

በምስሉ ላይ የምናያት እህታችን ሀና ሙሉጌታ ትባላለች።
ይህች ፍልቅልቅ የ22 ዓመት ወጣት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪ ስትሆን ከ3 ዓመት በፊት ባጋጠማት የመተንፈሻ ላይ ኢንፌክሽን ምክንያት በመቀሌ (አይደር ሆስፒታል) እንዲሁም በጳውሎስ እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታለች።

በዚህም ወላጆቿ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ፣ ገንዘባቸውን ተጠቅመው ኃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተው ነበረ።

ዛሬ ላይ ግን ለግላጋዋ ወጣት ሀና ከቤተሰቦቿ አቅም በላይ የሆነ ነገር ገጥሟታል።
የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ከታከመች 85 በመቶ የመዳን ተስፋ እንዳላት ነግሯታል።

ለጋላጋዋ ወጣት ሀና ሙሉጌታ የተባለውን ያህል ገንዘብ የመክፈል አቅም ስለሌለኝ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ወደ ምትኖሩ ወገኖቼ እጄን ለመዘርጋት ተገድጃለሁ ትላለች።

ተወዳጇ እህታችን መማር አለባቸው ይህን በጎ ስራ ለመስራት ቆርጣ ተነስታለችና ከጎኗ እንቆም ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ ውድ ወገኖቻችን በተለመደው የበጎ ስራ አርበኝነታችሁ የሀና ሙሉጌታን ህይዎት እንደምትታደጉ አንዳች ጥርጥር የለኝም።

መርዳት የምትፈልጉ፦ በወላጅ አባቷ በተከፈተ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000416887587 ሙሉጌታ አዳነ ብለው ገቢ ያድርጉ።