Get Mystery Box with random crypto!

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊት እና የአፍ ውስጥ የቀዶ ህክምና ተደራሽ ለማድረግ በማሰ | Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊት እና የአፍ ውስጥ የቀዶ ህክምና ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ከግንቦት 5 -12/2015 ዓ.ም ከካናዳ (ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ) በሚመጡ የፊት እና የአፍ ውስጥ ቀዶ ጥገና (oral and maxilofacial surgery) ስፔሻሊስቶች  ጋር በመተባበር  የቀዶ ህክምና አገልግሎት ስለሚሰጥ የሚከተሉትን የህክምና አይነቶች ችግር ያለባችሁ ታካሚዎች እንድትመዘገቡ እና የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናሳውቃለን፡፡

መመዝገብ የሚችለው የህመም አይነቶች፦

- የመንጋጋ መገጣጠሚያ እና የአፍ አለመከፈት ችግር
- የፊት አካባቢ የነርቭ ህመም
- የፊት አካባቢ እና የአፍ ውስጥ እባጮች ካንሰርን ጨምሮ
- የምራቅ አመንጪ እጢዎች ህመሞች
- የፊት እና የመንጋጋ አጥንት ስብራት
- የፊት አጥንቶች እድገት አለመመጣጠን እና የፊት መጣመም ችግር
- የፊት እና የመንጋጋ አጥንቶች በተፈጥሮዊና በጉዳት የሚከሰቱ የገጽታ ችግሮች
-የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር

መመዝገቢያ ቦታዎች፦

በጥቁር አንበሳ  ስፔሻሊዝድ ሆስፒታል ስኳር ማዕከል የጥርስ ህክምና ክፍል(1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ቁ.14------+251913895471 ዶ/ር  ፌቨን ወይም ዶ/ር ቀመር +251910056584
በአ.አ ዩኒቨርሲቲ  የጥርስ ህክምና  ማዕከል(6ኪሎ) -----0966138504 ዶ/ር ዘርይሁን
@tenamereja