Get Mystery Box with random crypto!

ይሀን አስተውላችሁት ታውቃላችሁ? ብዙ ጊዜ ትኩረታችን ማግኘት፣ማሳካት ላይ ነው፡፡ የአንድ ነገር | ተመስገን አብይ _ Psychologist

ይሀን አስተውላችሁት ታውቃላችሁ?

ብዙ ጊዜ ትኩረታችን ማግኘት፣ማሳካት ላይ ነው፡፡ የአንድ ነገር ባለቤት መሆን ላይ ነው፡፡

ነገር ግን :-
ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች አገኘን እንበልና እናስብ፡፡ ታዲያ ያገኘናቸው ነገሮች የኛ ሆነው ምን ያህል ጊዜ መቆየት የሚችሉ ይመስላችኋል?

ለማለት የፈለኩት ይህንን ነው :-

አንድን ነገር ከማግኘት ይልቅ ይዞ መቆየት ይበልጣል፡፡

ከዚህ በፊት አግኝተን የምናውቀው ገንዘብ፣ ስራ፣ ሰው... ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ ታዲያ ምን ያህሎቹ እስካሁን አብረውን ቆይተዋል? ምን ያህሎቹንስ አጥተናቸዋል?

ዋናው መልዕክቴ :-

አሁን ያለንን ማወቅ፣ መረዳት ቀጥሎም በተገቢው መንገድ እንዴት መጠቀም እንደምንችል ማሰብና መዘጋጀት ነው፡፡

አሁን ያለንን ለረጅም ጊዜ ሊጠቅመን በሚችል መልኩ አቅዶ መጠቀም በጣም የተሻለ ነው፡፡

@temuabiy @temuabiy @temuabiy @temuabiy