Get Mystery Box with random crypto!

የሃገራችን ተማሪዎች እና መምህራን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው የመማር ማስተማሩን ሂደት | telebirr

የሃገራችን ተማሪዎች እና መምህራን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲከውኑ ከ4.8 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል።

በዛሬውም ዕለት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ እና የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚረዳ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ለዚሁ ተግባር በተዘጋጁት በአጭር መልዕክት 9222 በቴሌብር የመለገሻ ቁጥር 9222 እና ውጪ ሃገራት የምትኖሩ ድጋፍ ሰጪዎች በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ መላኪያ 993161616 አቅማችሁ የፈቀደውን ገንዘብ በመላክ ድጋፍ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን::

ለተጨማሪ መረጃ https://bit.ly/3gAxX7Z ይጎብኙ