Get Mystery Box with random crypto!

የቴክኖሎጂ አጋራችን ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በአድዋ ድል | telebirr

የቴክኖሎጂ አጋራችን ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡

ልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ የስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን ልማትን እና ቱሪዝም የመሳሰሉት የስማርት ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ በቀረቡት የዲጂታል ሶሉሽኖች እና በአመራሩ ብቃት መደነቃቸውን የገለጹ ሲሆን ኩባንያችን ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን እየተጫወተ ያለው ሚና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU #Ethiotelecom #telebirr