Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር የ | telebirr

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር የተመራ የከፍተኛ ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡

ለልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ በቀረበው ዓውደ-ርዕይ የሀገራችንን የቴሌኮም አገልግሎት ጉዞ እንዲሁም ኩባንያችን ለማህበረሰባችን፣ ለቢዝነሱ እና ለተቋማት የሚያቀርባቸው ዲጂታል ሶሉሽኖችን ላይ በተግባር የተደገፈ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመጨረሻም ኩባንያችን በገነባው ሰፊ መሰረተ ልማት በመጠቀም የዲጂታል ሶሉሽኖችን በስፋት በማቅረብ በማሕበረሰባችን ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጣ እንዲሁም የተቋማት እና ቢዝነሶች አሰራር በማዘመን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረጉን ጉዞ ለማፋጠን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተገልጿል፡፡


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia