Get Mystery Box with random crypto!

ኩባንያችን ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር የስማርት ክላስሩም ሶሉሽኖች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለመተ | telebirr

ኩባንያችን ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር የስማርት ክላስሩም ሶሉሽኖች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለመተግበር የሚያስችል ስምምነት በዛሬው ዕለት አደረገ፡፡

ስምምነቱ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በስምንት አዳሪ ት/ቤቶችና በ33 ልዩ ትምህርት ቤቶች 82 ስማርት የመማሪያ ክፍሎችን እና አስፈላጊ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት አዘጋጅቶ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ይህም የትምህርት አሰጣጥ ስርዓቱን በማዘመን ጥራት ለመጨመር፣ ወጭን ለመቀነስ እና ትምህርትን በዲጂታል መንገድ በቀላሉ ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ ትምህርትን ለዜጎች አካታች እና ተደራሽ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን የትምህርት ግብዓቶች እጥረትን ለመቅረፍ፣ ትምህርትን ተማሪ ተኮርና አሳታፊ ለማድረግ እንዲሁም የተግባር ትምህርቶችን በስማርት ቤተሙከራ በማቅረብ ብቁ ትውልድ ለማፍራት ያስችላል፡፡

ኩባንያችን ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከሸገር ከተማ እና ኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑ እንዲሁም የዜጎችን የዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ የሚያሻሽሉ የዲጂታል ሶሉሽኖችን እና መሠረተ-ልማቶችን በማቅረብ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል።

ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/3PLQ7Wp ያንብቡ

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU