Get Mystery Box with random crypto!

ጠባሴ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tebasemidea — ጠባሴ ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tebasemidea — ጠባሴ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @tebasemidea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 177
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ሚዲያ ለጥበበኞች የተከፈተ
:- ግጥሞች
:- ሙዚቃ
:-ፎቶ ግራፍን ጨምሮ
የተለያዩ መዝናኛዎችን ሁሉን በአንድ የሚገኝበት ቻናል ነዉ
📚📝📖 የተሻለ ትውልድ ለተሻለች ኢትዮጵያ!!

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-21 11:24:01 @Natnaelnet
77 views ☞net, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:05:23 ሰው የሚከፈተውም የሚዘጋውም አንተ በተከፍትከው እና በተዘጋኸው ልክ ነው!!
ልብህን ዘግተህ የሌላው ልብ እንዲከፈት አትፈልግ!
92 views ☞net, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 12:54:26 በራሷ ደስተኛ ያልሆነች ሴትን ለማስደሰት አትልፋ! አለምን ሁሉ ብትሰጣትም መቼም አታስደስታትም!
-
ከቻልክ በራሷ የምትደሰትበትን መንገድ ጠቁማት!
93 views ☞net, 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 22:06:22 "ጠልተኸኛል አይደል ?" አለቺኝ እንባ ባቀረሩ አይኖቿ አይኔን እያየች....

እንደ እውነቱ ከሆነ መልሱን አላውቀውም
ምን ልበላት?

አዎ ጠልቼሻለሁ !
እኔ ትልቅ ቦታ የምሰጣቸው ነገሮች ላንቺ ኢምንት ሆነው ስለምታጣጥያቸው ጠልቼሻለው!...ውድ ሐሳቦቼን ስለምታራክሽብኝ ጠልቼሻለሁ!...ለልፋቴ ምንም ዋጋ ሳትሰጪ እኔን ለመተቸት ትንሹን እንከኔን የተራራ ያህል ስለምታገዝፊ ጠልቼሻለው!...ከቸልተኝነት ይሆን ካለማወቅ ባልገባኝ መንገድ የእኔ ህይወት ላንቺ በጣም ቀላል መስሎ ስለሚታይሽ ጠልቼሻለሁ!
ልበላት?(ይሄም እውነት ነው።)


ቀና ብዬ ገረመምኳት የዘገየው መልሴ ይበልጥ ተስፋ አስቆረጣት...ተገድቦ የቆየው እንባዋ በጉንጮቿ ወረዱ...አሳዘነቺኝ...እንባዋ ውስጤ ይንቦገቦግ የነበረውን የንዴት እሳት አጥፍቶ አቀዘቀዘኝ...በጎ ነገሯ ታሰበኝ የዋህነቷ፣ለእኔ ያላት ፍቅር...ለድርድር እንደማታቀርበኝ...ለእኔ ብዙ እንደሆነች ታወሰኝ። (ይሄም እውነት ነው።)

ወደ ደረቴ አስጠግቼ አቀፍኳትና ስትጠብቀው የነበረውን ምላሽ ሰጠዋት...

አ ል ጠ ላ ሁ ሽ ም! (ከአንቺ ለመሻል ይሄን እውነት መረጥኩ።)


ከተቀደደው ማስታወሻ
112 views ☞net, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:30:46 , ለህይወቴ ትርጉም የሰጠችው እሷ ነች ብዬ አምን ነበር...በሷ ፍቅር ክንፍ ባልኩበት ወራት...የሰው ልጅ ለመኖር ምን ያስፈልገዋል ቢሉኝ...ምግብ፣ውሃ፣መጠለያ እና እሷ እል ነበር...ለእኔ ያን ያህል ታስፈልገኝ ስለነበር...

ሌት ተቀን ከእርሷ ሐሳብ ውጪ ሌላ ሐሳብ አልነበረኝም...የእኔን ሕይወት እርግፍ አድርጌ ትቼው የእርሷን ሕይወት ደባል ሆኜ የምኖርላት ይመስል ነበር...በእያንዳንዱ ነገሯ እጨነቃለሁ...

ታዲያ ይሄ ለእርሷ የገባት ጊዜ ችግር ሆነ...በእኔ ሕይወት ውስጥ ያላት ቦታ ሲገባት በእርሷ ሕይወት ውስጥ ቦታ ነፈገችኝ። እንደ አንድ ተራ እቃዋ እንኳን አልቆጥረኝ አለች...ነገር ተበላሸ።ሲሻት ከሕይወትህ ወጥቻለሁ ትላለች...እኔ እታወካለው...እናቶቻችን የሚያመልኩትን የሚለምኑትን አይነት ልመና እለምናታለሁ...የማንም ሁኚ ብቻ አትራቂኝ እላታለሁ። ከእኔ ለመራቅ የሞከረቻቸው እድሎች አልሳካ ሲሏት ትመለሳለች። በደስታ እቀበላታለሁ። ይህ ነገሯ ተደጋገመ! ስትሄድ ስለመናት፤ስትመጣ በደስታ ስቀበላት...ሰነበትን እና መንገድ የሆንኩ መሰለኝ...ወዴት እንደምወስድ ባላውቅም።


አንድ ቀን ልንዝናና ከተቀመጥንበት ቦታ እንዳለን...አጠገቤ በመኖሯ እንደንጉስ ተጀንኜ በኩራት በተቀመጥኩበት...እንደለመደችው ሳትመጣ "ልሄድ ነው" ብትለኝ...ኩስስ አልኩ።ተረጋግቼ ይሄ የመጨረሻዋ እንደሚሆን ለራሴ ማልኩለት።ከእንግዱህ በሬን ብታንኳኳ ላልከፍትላት ማልኩ...በእልህ ወደ ጆሮዋ ተጠግቼ እንዲህ አልኳት...


<መንገዱን ታውቂዋለሽ ወይስ ላሳይሽ?!>


ከተቀደደው ማስታወሻ
ናቲ
125 views ☞net, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 19:54:42 አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-

"የእርጅና ወራት ሳይመጣ በጉብዝና ወራት ፈጣሪህን አስብ!" የተባልከው እውነት ነው::
-
በፍቅር አምላክህን ካላሰብከው በህመም ታስበዋለህ::
-
ነፃ በሆንክ ሰዓት ያልጠራኸውን በእስር ስትወድቅ ተጠራለህ::
-
በጤና ያፈለከውን ስትታመም ትፈልጋለህ::በሰላም ያላዋራኸን አዳጋ ሲያጋጥምህ ታዋራለህ::
-
ሰዓቱ ደርሷል::አሁንም የመዳንህን እድል አታባክነው::በምድር ቅዠት ተኝተህ የአምላክህን መንግስት አትለፈው::
-
ምድር እንደሆነች ከጊዚያዊ እርካታ ውጪ የምትሰጥህ አንዳች የላትም::የሰጠችህንም ነገር አንድ በአንድ ቆጥራ ስትሞት ትቀበልሃለች::
-
ማንም ሰው ሊነጥቅህ የማይቻለውን መንፈስህን ብቻ ፈልገው::ነፃ የምትወጣው በእርሱ ነው::
-
አምላክህን ብትውደው ጊዜ እና ትኩረትህን በሰጠኸው ነበር::ድምፁን ለመስማት እና የአብሮነት ጊዜን ለማሳለፍ በተመኘህ ነበረ::
-
ነገሩ የማያውቁት አገር አይናፍቅም ሆኖል::በአለም አስትዳደግ አምላክህን እንድትረሳ ተደርጏል::ጠረኑ: ደግንቱ: ውበቱ: እርዳታው እና ቸርነቱ ጠፍቶሃል::አለም አታልሎህ ውስዶሃል::
-
እርሱ ግን ይወድሃል እና መቼም አይተውህም::ብትጠላው አይጠላህም::ህጉን ብታፈርስም አያፈርስህም::
-
ጠባዩ ሙሉ ፍቅር ነውና እስከ መጨረሻው ያፈቅርሃል::በፍቅር ካልሰማኸው በህመም ቢሆን እንድትቀርበው ይስብሃል::
-
አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-
እስቲ ደስስስ ይበለው ስማው::ልብህን ወደ እርሱ መልስ::የቀድመ የአባት እና የልጅ ፍቅራችሁን አድስ::እስቲ አንተ በትራህ አምላክህን ደስስስስ አሰኘው::ልቡን አብራላት::የፍቅር: የይቅርታ እና የሰላም ሰው ሁንለት::
-
148 views ☞net, 16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 22:18:49 ደመና የፀሐይን ብርሃን እንደሚጋርድ ክፉ ሀሳብም የአምላክን ፍቅር ይጋርዳል::
-
አምላክ ባንቺ አንቺ ውስጥ ሲሆን አንቺ ደግሞ በአምላክ ውስጥ ሁኚ::
-
እንቺ እሱን እንደምትፈልጊው እርሱም አንቺን እንደሚፈልግ እወቂ::የጠፉ ልጆቹን የምታድን መሳርያው ሁኝለት::
-
የአለም መከራ "የአምላክ ፍቅር ለምን ራቀን?"ሊያብልሽ ይችላል::የአምላክ ፍቅር ርቆ ሳይሆን በክፉ የሰው ልጆች ሀሳብ ተጋርዶ እንደሆነ እወቂ::
-
አለም ከመፈጠሯ አስቀድሞ የነብረ የህይወት የተገነባበት መሰረት የአምላክ ፍቅር ነው::ከአለም በኃላም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ሀይል ነው::
-
ይህንን የፍቅር ሀይል በግልሽም ሆነ በአለም ህይወት ካላየሽው በክፉ ሀሳብ ተጋርዶብሻል ማለት ነው::አምላክ ባንቺ አድሮ አንቺንና ልጆቹን እንዳያድን ክፉ ሀሳብ ጋሬጣ ሆኖብሻል::
-
ለምሳሌ ባንቺ ውስጥ ምን አይነት ሀሳቦች አሉ? እርግጥ ነው የገጠመሽ መጥፎ ነገር አለ::እርግጥ ነው ሰው በድሎሻል::እውነት ነው መሆን አልነበረብትም የሚያስብል ክፉ ነገር ገጥሞሻል::
-
በክፉ ገጠመኝ ምክንያት በውስጥሽ ያዘልሻቸው ክፉ ሀሳቦች መልካሙን የአምላክ መንፈስ እንደሚጋርዱ እወቂ:: ባለማወቅ የሰው ልጆች በልባችን የምናስባቸው የሀጥያት እና የክፋት ሀሳቦች የአምላክ ብርሃንን ጋርደውብን ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል::
-
ፈጣሪሽ እረኛሽ ከሆነ የሚያሳጣሽም የለም::ከሰውም ሆነ ከአለም አዲስ ነገር መጠበቅ አቁሚ::የሁሉም ነገር ምንጭ ከሆነው እርኛስ አምላክ ጋር ግንኙኑት ፍጠሪ::
-
ግንኙነቱ የሚጀምረው ሀሳብን በማፅዳት ነው::ይህም ይቅርታ ወይም ንስሃ ይባላል::ለዘመናት በልብሽ ሲንከባለል የመጣው መጥፎ ሀሳብ ሲወጣ መልካሙ የአምላክ መንፈስ መግባት ይጀምራል::
-
ይህ ቀላል ሂደት አይደለም::እያንዳንዱ ክፉ ሀሳብ ለብዙ ዘመን ባንቺ ውስጥ ስለኖረ በቀላሉ አይለቅሽም::ግን ቀላል የሆነውን አምላክ በፍፁም እምነት እና ፅናት ብትጠይቂው ያደርግልሻል::
260 views ☞net, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 01:29:43 "ከአንድ ሚሊዬን ብር እና ከአንድ ሙዝ የቱ ይሻልሻል?" ተብላ ጦጢት ብትጠየቅ ምርጫዋ አንዱ ሙዝ ነው::
-
አንድ ሚሊዬን ብር ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አታውቅምና:
-
"አሁን ተቀጥሮ ደሞዝ ከማግኘት እና አሁን ደክሞ ወደፊት የሚያተርፍ ቢዝነስ ከመጀመር የቱ ይሻላል?" ተብሎ ቢጠየቅ የብዙ ሰው ምርጫ
መቀጠር ነው::

-
ሪስክ ወስዶ ቢዝነስ መጀመር ከመቀጠር የበለጠ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ብዙ ሰው አያውቅምና::
-
አለማወቅ የወድቀት ሁሉ መሰረት ነው::አእምሯችን እውቀት አልባ ከሆነ ህይወታችን ፍሬ አልባ ይሆናል::መንፈሳችን ጥበብ ከሌለው ልፋታችን ስኬት የሌለው ይህናል::
-
ህይወት በብዛት የምትሰራው በጥበብ እንጂ በጉልበት አይደለም::በተለይ ባለንበት ዘመን የስኬት መግቢያ በሩ እውቀት እና መረዳት ነው::
-
ስለህይወት ምን ያህል ታውቃላችሁ? ሰዎች እንዴት ይሰራሉ? ገንዘብ ራሱ ምንድን ነው? የትዳራችሁን ደስታ ለመጨመር ምን ማወቅ አለባችሁ? ለደስታ : ለሰላምና ለፍቅር ሚስጥሩ ምንድን ነው?
-
ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎችም ሆነ ለማንኛውም የምድርና የሰማይ ኑሮ አስፈላጊ እውቀት አለ::ይህንን እውቀት ከእጁ ያስገባ የህይወት ሚስጥር ከእጁ ያስገባ ነው::
-
የራስ እውቀት ላይ የሚደረግ ኢንቬስትመንት አዋጭ ነው::ትርፉም ያረካል::እውቀት መቼም ሊጠፋ የማይችል ሀብት ነው::እውነተኛ እውቀት ያለው እውነተኛ ሀብታም ነው::
-
በጉልበት ከመኖር በእውቅት ወደ መኖር ተሸጋገሩ::
የምትፈልጉትን ነገር ወደ እናንተ የሚያመጣውን እውቀት ተማሩ::ዝም ብላችሁ ያገኛችሁትን "እውቀት!" ወደ ውስጥ አታስገቡ::እውቀታችሁ ከአላማችሁ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ይሁን::የወደዳችሁትን ነገር ወደ እናንተ የማያመጣ እውቀት ይቅርባችሁ::እያወራችሁ ብቻ የምትጎርሩብት እውቀት አለማወቅ ነው::
-
ማወቅ እውቀቱን ተግብሮ ውጤት ማምጣት ነው::
298 views ☞net, 22:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 15:14:58 ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት


እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፥ የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
ከሶስት አመት በላይ
እየተሰበርን ፣ " ሰበር" በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
ግፍኛን ተቃውመን ፣ ግፈኛን ደግፈን
ደብዳቤ እየላክን ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በስጋት ፣ እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ግዜ
ቁርስ ምሳና ራት ፣ መከራ ስንበላ
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እንደምነህልን ፣ ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"ስልታዊ ማፈግፈግ" ፣ በሚል ፍልስፍና
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ እልፎች ሚደግፉህ
እልፎች ሚያወድሱህ ፣ እልፎች የሚነቅፉህ
እንዴት ነው መንግስትህ
ከአዲስ ምእራፍ ጋር ፣ የተመሰረተው?
አንድ አንተን ለማፅናት ፣ ስንቶች ነን ምንሞተው?
#ሼርርር

@tebasemidea
@tebasemidea
@tebasemidea
1.0K views ☞net, 12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ