Get Mystery Box with random crypto!

#Update በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን ብሄራ | ታማኝ ዜና

#Update

በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

“ የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል ” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ / አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ~ tikvah

@tamagnzena @tamagnzena