Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት ባህርዳር ከተማ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል።አባይ ድልድይ ሻሁር እየወሰዱ የነበሩ ሦስት ወጣቶች | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት ባህርዳር ከተማ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል።አባይ ድልድይ ሻሁር እየወሰዱ የነበሩ ሦስት ወጣቶችን ተኩሰው ገደሉ። አባይ ወንዝም እንደ እንጨት እያግተለተለ ወስዷቸዋል። አንድ ከመራዊ የመጣ አባት ቀበሌ 14 ላይ የ4 ዓመት ህፃን ልጁ ተገድሎ አባትዬው አቅፎ "ልጄን፥ ልጄን" እያለ እያለቀሰ ሲዞር ውሏል። አባይ ማዶ ሰማዕታት ፊት ለፊት አንዲት መጫትን በእንጨት አልጋ ይዘው የሚሄዱ ሰዎች በአደባባይ ተረሽነዋል። ተሸካሚዎች አራቱ፣ መጫቷንና ገና ከተወለደ አንድ ቀን የማይሞላውን ጨቅላ ተገድለዋል። እዛው አባይ ማዶ አየር ጤና አካባቢ ሁለት ወጣቶችን ድንጋይ አንሱ በማለት ደረታቸው በጥይት ተመትቶ ተገድለዋል። ቀበሌ 3 ሊስትሮ ይሰራ የነበረ ሙስሊም ሰውየ ለአራት ልጆቹ ደረቅ እንጀራ ፍለጋ ላስቲክ ይዞ እንደወጣ ገድለውታል።

የተባበሩት ስጦታ ሥጋ ቤት አካባቢ አንድ ሰውየ ይገደላል። ልጅ ያዘለች ሚስቱ እየጮኸች ስትሄድ እሷንም ገደሏት። ህፃን ልጃቸው እየሮጠ ሲመጣ እሱንም ደገሙት። አስክሬኑ ሲነሳ የታዘለው ህፃን እስትንፋሱ አለ። አልሞተም። በተመሳሳይ በተለምዶ ዲፖ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ አባት የህፃን ልጁን ይዞ ሲሄድ ህፃኑንና አባትዬውን ተኩሰው ገድለዋቸዋል።
ወጣቶች ለማንሳት እየሮጡ ሲሄዱ ተኩሰውባቸው ሬሳው ሳይነሳ ውሏል።

የሆራይዞን ትምህርት ቤት ባለቤት የሆነውን የ26 ዓመት ልጁን ልደታ ሰፈር ከቤት ገብተው እረሽነውታል። እዛው ልደታ ሰፈር የቤት ለቤት እረሸና ተፈጽሟል። አንድ ሰውየን ከውጭ አንበርክከው ከውስጥ ያለችውን ሚስቱን ደፍረዋታል። ቤት ለቤት በሚያደርጉት ፍተሻ ከአንገት ሀብል እየበጠሱ፣ ሞባይልና ላብቶፖ እየቀሙ ወስደዋል። ምንም የማያውቁ የቆሎ ተማሪዎች ተገድለዋል። ባጠቃላይ ከትጥቁ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ከ700 በላይ ንፁሐን ተጨፍጭፈዋል። ልደታ ማርያም ከ54 በላይ፣ አቡነ ሐራ ቤተክርስቲያን ከ46 በላይ፣ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ36 በላይ ሰዎች ያሉበት የጅምላ መቃብር ተፈጽሟል።

እርምጃ ተወስዶባቸው በደም የተበከሉና ዝንጥልጥላቸው የወጣ አስክሬኖች በመስቀለኛ መንገዶች ላይ፣ በዋና አውራ ጎጃናዎች ላይ፣ እቤቶች አጠገብ ላይ ተጥለው የሬሳ ኤግዚቪሽን ታይቷል። የህዝቡን ስነልቦና ለመጉዳት ሬሳ ሳይነሳ ሦስትና አራት ቀን ቆይቷል። ባጠቃላይ
በባህርዳር የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ እና እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት (grave violation of human rights) ለዐማራ ከልክ በላይ ያላቸውን ጥላቻ ያሳዩበት ነው። አሁንም ግድያው አልቆመም። ሰዎች እየተገደሉ የትም እየተጣሉ ናቸው። በየጥሻው፣ በየበቆሎው ተገድሎ የተጣለ ሬሳ እየተገኘ ነው። ባህርዳር የሚታየው ነጠላውን ዘቅዝቆ ለቅሶ ለመድረስ የሚመርመሰመስ ሰው ነው። አንድ ሰው በቀን ቢያንስ በእግሩ ከአራት እና ከአምስት በላይ ለቅሶ ቤት ይደርሳል። በየቦታው ሀዘን ነው። በየቦታው መከፋት ነው።

አሁንም ከሰኞ ጀምረን ቤት ለቤት ፍተሻ እናደርጋለን እያሉ ናቸው። አሁንም ንፁሐን ይገደላሉ። ንብረት ይዘረፋል። ሴቶች ይደፈራሉ። "በለው" ነው። "ተኩሰበት" ነው። አንድ ወታደር ርችት እንደመተኮስ ያህል ጥይት ተኩሶ ንፁሐንን ያጋድማል። ተጠያቂ የለም፤ ጠያቂም የለም።

እንዲህ ያሉ ግፎች እንዳይዘገቡ ኔትወርክ ተዝግቷል። ይህን የምንጽፈው በሞት ቀለበት ውስጥ ሆነን ነው። ከህዝባችን የሚበልጥ የለም በሚል ነው። መረጃውን በቲዊተር፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በምታገኙት አጋጣሚ እንድታሰራጩ እጠይቃለሁ።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut