Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ይህን የምጽፍላችሁ በባሩድ ጭስ ውስጥ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት ባህር ዳር በቅርብ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ይህን የምጽፍላችሁ በባሩድ ጭስ ውስጥ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት ባህር ዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘው "ጉብሪት" ላይ ሄሊኮፍተር አውርዳቸው የሄደችውን ወታደሮች ፋኖ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በተመሳሳይ በኮሎኔል ጌታው መኮነን የሚመራው አያሌው መኮነን የፋኖ ብርጌድ ከ30 በላይ የፌዴራል ፖሊሶችን ከባህርዳር 65 ኪ.ሜ. ቁንዝላ ከተማ አካባቢ ከነመሣሪያቸው ማርኳል። ፋኖ አያሌው ብርጌድ በድል እየገሠገሠ ይገኛል።

-ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ የኦህዴድ ብልፅግና ሠራዊት ባህርዳር ከተማን የጦር አውድማ አድርጓታል። ንፁሐን በየቦታው
ጨፍጭፏል። የተባበሩት አካባቢ መትረየስ ጠምደው ከተማውን እያረሱት ይገኛሉ። ከላይ ከደንባቄ ተራራ ቁልቁል ወደ ከተማዋ ከባባድ የመድፍ ቅምቡላ እየወደቀ ነው።

-ፋኖ የሚችለውን እያደረገ ነው። 50 ዓመት በሙሉ ሲሳደድ፣ ሲፈናቀል፣ በጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክስት ሲከሰስ የኖረውን የዐማራ ህዝብ ፈጽሞ ከመጥፋት ለማዳን ደሙን እያፈሰሰ፤ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው። በከፍተኛ የአሸናፊነት ስሜት (Sense of invincibility) ወደፊት እየገሠገሠ ነው። እንደ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ "...ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ" እያለ መድፉን፣ መትረየሱን፣ ቦንቡን ጥሶት እያለፈ ነው።

"የዘሜ ታናሽ ተላይነህ ወንዱ
በልቡ አስተኛው በየመንገዱ" እያለ በመፎከር ላይ ነው።

-አሁን ባህርዳር ሁለት ችግር ብቻ ናቸው ፈተና የሆኑት። የመጀመሪያው ኦህዴድ ብልፅግና በኮማንድ ፖስቱ ያደራጃቸው የቀበሌ፣ የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ካድሬዎች መረጃ በመስጠት፣ በማሳበቅ ባንዳነታቸውን በሚገባ እያስመሰከሩ ነው። ለነዚህ ካድሬዎች የዐማራ መፈናቀል፣ መሞት፣ መሰደድ ጉዳያቸው አይደለም። ዛሬ ታማኝነታቸው አረጋግጠው ነገ የሥልጣን እድገት እናገኛለን ብለው በተስፋ የሚኖሩ ከንቱዎች ናቸው።

ሁለተኛው በአሁኑ ሰዓት ለከተማው ህዝብ ፈተና የሆኑት ስግብግብ ነጋዴዎች ናቸው። በእያንዳንዱ የምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዋጋ በመጨመር ከአገዛዙ ባልተናነሰ ሁኔታ ህዝቡን እያስመረሩ ስለሆነ ሊያርፉ ይገባል። ሲሆን ይህን ችግር በጋራ ለመሻገር ቢተባበሩ ጥሩ ነበር፤ አለበለዚያ ግን በምግብ አቅርቦቶች ላይ ከፍተኛ ዋጋ መጨመር አገዛዙን እንደማገዝ ይቆጠራል። ዛሬ ከጥዋቱ ጀምሮ በውሸት ውሃ ተበክሏል ብለው ያስቀመጡትን ምርታቸውን ሲሸጡ አርፍደዋል። ከዚህ በላይ ነውር፣ ለህዝብ ደንታቢስነትና ስግብግብነት የለም። መቆም አለበት።

የድል ዜናዎች ተዘርዝረው አያልቁም። ባጭሩ ግን ሁሉም አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርግ። ብልፅግና ያሰማራቸው ሌቦች የፋኖን ስም ለማጠልሸት ስለተሰማሩ ሁሉም አካባቢውን ነቅቶ ይጠብቅ። በየአካባቢው ይደራጅ። ይህን ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሥልጣኔ፣ ፀረ-ሰው አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም ሁሉም ሚናውን መወጣት አለበት።

ድል ለዐማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ!


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut