Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ይህ ፍም እሳት #ደብረማርቆስ ነው። በርግጥ የጎጃም ዐማራ ለጭቆና አገዛዝ ተመችቶ አ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ይህ ፍም እሳት #ደብረማርቆስ ነው። በርግጥ የጎጃም ዐማራ ለጭቆና አገዛዝ ተመችቶ አያውቅም። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ዘውድ ያነቃነቀው የጎጃም ገበሬዎች አመፅ ነው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የብቸናን አመፅ ለማዳፈን ከሰማይ ቦንብ ነበር ያወረደው። ደርግን ያርበደበዱት የቢቸና አርሶአደሮች ነበሩ። ደርግ አመፁን ለማዳፈን ጎጃምን በአውሮፕላን ደብድቦታል። በ1966 ዓ.ም. በደርጉ ሻለቃ እንዳለ ተሰማ የተመራው የደርግ ሠራዊት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የቢቸና አርሶ አደሮችን ጨፍጭፏል።

ሀገሩ የግፉን ቀንበር መሸከም የማይችል የእነ በላይ ዘለቀ፣ የነአዳብሬ ዳርጌ፣ የነደጃዝማች አበረ ይማም ሀገር ነው። ኩሩ (proud)፣ ክቡር (dignified)፣ በራሱ የሚመካ (self-reliant) የዐማራ ህዝብ የሚኖርበት።

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ዘመን በባሕርዳር ሜጫ ዙሪያ አካባቢ የ"ቀላድ" መጣልን በመቃወም የተነሳውን አመፅ የመሩት ደጃዝማች አበረ ይማም በዚያን ወቅት ለአገሬው ያሰሙት ቀስቃሽ ንግግራቸው እንዲህ የሚል ነበር፣

"አገሬ ጎጃም መሬትህ ሲለካ ዝምብለህ ታያለህ እኔ ምንም የጎደለብኝ ነገር የለም። ከሐብቴ ብዛት የተነሳ በአንድ ቀን ሐምሳ ላሞች ወልደው የደስደስ ብዙ መትረየስ ጥይት እንደተኮስኩ ታውቃለህ። አሁን የተነሳትሁት አገሬ ሲበደል ዝም ብዬ አላይም ብዬ ነው። ተነስቻለሁ ተነሳ፤ ወጥቻለሁ እና ውጣ" (የአማራ ሕዝብ ታሪካዊና ባህላዊ አሻራዎች፣ 67)

ወንድሜ ...ጎጃም የነ ውባለ ተገኑና በባምላኩ አየለ ሀገር ነው። በ1967 ዓ.ም. በተካሄደው የብቸና አውራጃ ገበሬ አመፅ የመራው ውባለ ተገኑ ነበር። በተደጋጋሚ ከደርግ ታጣቂዎች ጋር እየተፋለመ ብዙ የደርግ ታጣቂዎችን ደምስሷል። በመጨረሻም በሚያዝያ ወር 1972 ዓ.ም. ውባለ ተገኑ እና ተከታዮቹ ተከበው ከደርግ ታጣቂዎች ጋር ሲዋጋ፣ ሶማ ቆላ፣ ከሶማ አቦ በስተሰሜን ከምትገኝ አንዲት ሸጥ ውስጥ እሱ፣ ሁለት ወጣት ልጆቹ ፣ ከሌሎቹ ግብረ አበሮቹ ጋር ተገድለዋል። ውባለ ተገኑ እና ልጆቱ በደርግ ጥይት ሲሞቱ የሶማ አቦ አካባቢ ኗሪ እንዲህ አለ።

"ሶማ ከበረሃው ውሃ የለም ሲሉ፣
ውቤ እና ልጆቹ ሲዋኙበት ዋሉ።"
(ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስ አበባ፣ ገጽ፣ 118-120)

በተጨማሪም፣ በብቸና የተደረገውን ፀረ ደርግ እንቅስቃሴ ከመሩት የብቸናው ባምላኩ አየለ አንድ አይና ጀግና መሪ ስለነበሩ፣

"በአምላኩ አባ ጊዮን የበረሃው መናኝ
በአንድ አይኑ ፀዳቂ በሌላው ተኮናኝ" ተብለው ተወድሰዋል። (የአማራ ሕዝብ ታሪካዊና ባህላዊ አሻራዎች፣ ገጽ፣ 72)

እና ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ ጭቆናን፣ የግፉ አገዛዝን፣ ባርነት በመፀየፍ የጎጃም ዐማራ ህዝብ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ዘውድ ያነቃነቀ፣ ደርግን ያርበደበደ፣ ወያኔን የተፋለመ ኩሩ ህዝብ ነው። ትናንት የንጉሡና የደርግ ተዋጊ ሂሊኮፍተር ያላቆመው ህዝብ ዛሬም በንጉሥ ተክለሃይማኖት አደባባይ "ከልዩ ኃይሉ ጎን ነን" እያለ ይገኛል።