Get Mystery Box with random crypto!

'ሌባ እና ሌባ' የተሰኘ ጉደኛ ፊልም ነገ ቅዳሜና እሁድ በባህርዳር ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

"ሌባ እና ሌባ" የተሰኘ ጉደኛ ፊልም ነገ ቅዳሜና እሁድ በባህርዳር ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል ይታያል። ፊልሙ ሁለት አይነት ፐርፐዝ አለው። "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" እንዲሉ የመጀመሪያው የከተማዋን የፊልም እንዱስትሪ ማነቃቃት፤ ሁለተኛው ደግሞ ከፊልሙ እይታ ከሚገኘው 10 ፐርሰቱን ለህፃን መክሊት መኮነን የህክምና ውጪ እንሚውል ፊልሙን ያስመጣው አቤኔዘር ይህአለም አስታውቋል።

ህጻን መክሊት መኮነን የ8 ዓመት ልጅ ስትሆን ትውልድ እና እድገቷ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 10 ነው። በ6 ዓመቷ በደረሰባት ድንገተኛ የጤና እክል ምክንያት ወደ ጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ተልካ ክትትል ስታደርግ ብትቆይም የህክምና ውጤቷ መቅኔዋ በሰውነቷ ያሉ የደም አይነቶችን ማምረት ባለመቻሉ ላለፈው 1 ዓመት ከ7ወር ተጨማሪ ደም በሳምንት ሁለት ጊዜ ስትወስድ ብትቆይም ለውጥ ባለማሳየቷና ሁለቱም አይኖቿ ማየት ከተሳናቸው 1 ዓመት ከ6 ወር ሆኗታል። በተጨማሪም በአፍንጫዋና በድዷ ላይ ደም እየፈሰሳት ስለሆነ የመቅኔ ንቅለ ተከላ እንድታደርግ ስትከታተልበት የነበረው የጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ቦርድ ወስኗል፡፡ "የሌባ እና ሌባ" ፊልም 10 ፐርሰንት ለዚህ ተግባር ነው ይውላል የተባለው። ቅዳሜ እና እሁድ ከፊልሙ ከመታደም ጀምሮ ህጻኗን ማገዝ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000531416736 (መሳይ መሰረት) ማገዝ ትችላላችሁ።

ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት
@Tadeletibebut