Get Mystery Box with random crypto!

ይህን እያደረጉ ያሉት ፋሽስቱ ዱቼ ሞሶሎኒ አሊያም ሶማሊያዊው መሀመድ ዜያድባሬ አይደለም፤ የቁረጠው | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

ይህን እያደረጉ ያሉት ፋሽስቱ ዱቼ ሞሶሎኒ አሊያም ሶማሊያዊው መሀመድ ዜያድባሬ አይደለም፤ የቁረጠው ፍለጠው ጌታ የዶክተር አብይ አሕመድ አገዛዝ ነው። እነዚህ ታሪክ አፍራሾች (Deconstructionists) እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኦሮሞ፣ ባልቻን ኦሮሞ፣ አትሌት አበበ ደምሴን ኦሮሞ፣ ፊውታራሪ ገበዬሁ ተክሌ ኦሮሞ በማድረግ ብቻ አላቆሙም፤
ወይንም የነፃነት ምንጭ፣ የዘላለም እሴት፣ የአውሮፓን የቅኝ ግዛት መመሪያ የበርሊን ጉባኤ የፈረካከሰውን የአድዋ ድል ህያውነት፣ አድማስ ዘለል ታሪክነት፣ የዓለም ነፀብራቅነት፣ አፍሪቃዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ደንገጡር በማድረግ
ብቻ አላቆሙም፤ ይሄው ዛሬ ደግሞ በአደባባይ ማክበር አትችሉም ብለው ከልክለዋል። ህዝቡን በጭስ በዱላና በጭስ እየበተኑት ነው። በአንጻሩ በመስቀል አደባባይ ደግሞ የዶክተር አብይ አሕመድን ፎቶ ይዘው እያከበሩ ይገኛሉ።

የራስ መኮንን ጦር ጀግንነቱን ያሳየበትን፣ ህመም ላይ የነበሩት ፊታውራሪ ገበየሁ እንደ ዝንጀሮ ገደል ለገደል እየተዘዋወሩ ዘንግ ይዘው ያዋጉበትን፣ ቀኛዝማች ታፈሰ በአንድ ጎራዴ የጠላት ሬሳ የከመሩበትን፣ መድፈኛው ራስ አባተ ቧያለው የጠላትን መድፍ በመድፉ የሰባበረበትን፣ እቴጌ ጣይቱ በብልሃት ጠላትን እጅ ወደላይ ያስባሉበትን የአድዋ ድል አታከብሩም የምንባልበት ግዜ ላይ ደርሰናል።