Get Mystery Box with random crypto!

እኔ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ልጅ በክርስትና ስሜ #ገብረሥላሴ የአባቶቼን ትዕዛዝ ሳላጓድል እፈ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

እኔ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ልጅ በክርስትና ስሜ #ገብረሥላሴ የአባቶቼን ትዕዛዝ ሳላጓድል እፈጽማለሁ።እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ብሰቀል፤ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ በድንጋይ ብወገር፤ እንደ ቅዱስ በርተሎሜዎስ አንገቴን ብቀላ፤ እንደ ቅዱስ ቶማስ በጦር ብወጋ፤ እንደ ቅዱስ ፊሊጶስ ተዝቅዝቄ ብሰቀል፤ እንደ ቅዱስ ማቴዎስ ብቃጠል፤ እንደ ካህኑ ዘካርያስ ቤተ መቅደስ ውስጥ ብታረድ ማተቤን አልበጥስም። ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ጾመ ነነዌን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ጥቁር ልብስ በመልበስ ጀምሪያለሁ።

አንድ ሲኖዶስ!
አንድ ፓትርያርክ!!
አንዲት ቤተክርስቲያን!!!
እጃችሁን ከቤተክርስቲያን አንሱ!