Get Mystery Box with random crypto!

በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ! የእንግጫ ነቀላና ከሴ አጨዳ በዓል በተለያዩ ዝግጅት መከበር ጀም | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ! የእንግጫ ነቀላና ከሴ አጨዳ በዓል በተለያዩ ዝግጅት መከበር ጀምሯል። የዐማራ ባህል መግለጫ የሚሏቸውን ለማስወገድ ላለፉት 40 ዓመታት ገዝግዘው ለመቁረጥ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። የዐማራው የቅርስ፣ የኩራትና የክብር ምንጭ፣ የታሪኩ ሞገስ የሆኑትን ቱባ እሴቶችን አስተዋሽ እንዳይኖራቸው፣ በተለይም ከመንግስታዊና ህዝባዊ የኪነ-ጥበብ መድረክ እንዲወገዱ፣ ጎልተውና ደምቀው እንዳይታዩ ከሚዲያ እንዲርቁ ተደርገው ቆይተዋል።

ዛሬ የተቋረጠውን በዓል ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ተገቢውን የሚዲያ ሽፋንም ሊሰጠው ይገባል።